ጉግል የአፍሪካን ብሮድባንድ ለማሻሻል ኢንቨስት ሊያደርግ ነው

ግንቦት 10፣ 2009

የወርልድ ባንክ አባል የሆነው አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጎግል ኩባንያ እና ሚትሲ ኩባንያ ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት የፋይበር ኦፕቲክ ኔትዎርክን ተደራሽነት ለማስፋፋት 100 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ኢንቨስት ለማድረግ መስማማታቸው ተገለፀ᎓᎓

ኢንቨስትመንቱ ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ያላቸውን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ችግርን ለማሻሻል የሚያግዝ ሲሆን ለኢኮኖሚ እድገትና ለተወዳዳሪነት ማነቆ ሆኖ የቆየውን የብሮድባንድ ችግር ይፈታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል᎓᎓

በዩጋንዳና በጋና የሚገኘውን የጎጉል ስራን ማስፋፋትና በሚቀጥሉት አምስት አመታት ብዛት ያላቸውን አዳዲስ ገበያዎችን የመፍጠር አላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ነው የተገለፀው᎓᎓

ኢንቨስትመንቱ የዲጂታል መሰረተ ልማት ኢኒሼቲቩ አንዱ ክፍል ሲሆን አላማውም በተጠቀሱት ሀገራት የኢንተርኔት ተደራሽነትን ማሻሻል ና ማስፋፋት ነው᎓᎓

የብሮድባንድ ትስስርን ማሻሻል የወርልድ ባንከ ቡድን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራው ስራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፤ አፍሪካን ቢዝነስ