የደቡብ ሱዳን አማፂያን የንፁሀንን ጉዳት ለመቀነስ ‹ ‹የሂ› ከተማን ለቀው ወጡ

ግንቦት 10፣ 2009

በያዝነው ሳምንት የደቡብ ሱዳን አማፂያን ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ ‹‹የሂ›› የተባለች ከተማን ለቅው መውጣታቸውን ገለፁ፡፡ 

የአማፂያኑ ጦር ከከተማው የወጣው በጦርነቱ በንፁሀን ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እንደሆነ የታጣቂው ቡድን ምክትል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፖል ላም ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ ተቀናቃኝ ሀይሎች መካከል በሌሎች ሶስት ከተሞች ላይ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑንም ተነግሯል፡፡

በዚህም ሂደት አብዛኛው የየሂ ከተማ ይዞታዎች በተቃዋሚ ሀይሎቹ ቁጥጥር እንደዋሉ ነው የተሰማው፡፡

አማፂያን ሃይሉ ከመንግስት ሃይሎች ጋር ቢሚያደጉት ፍልሚያ በቶክስ ልውውጥ ወቅት በመዲናይቱ የሚኖሩ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከተማውን ለቀው እንዲወጡ መናገራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ሱዳን ትሪቢዮን