በኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ለምስራቅ አፍሪካ ስጋት ፈጥሯል

ግንቦት 10፣ 2009

በሰሜን ምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተከሰተው ኢቦላ 3 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 6 ሰዎች ደግሞ ሆስፒታል ገብተው እየተረዱ ይገኛሉ፡፡

የተከሰተውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ከሩዋንዳ፣ ከኮንጎ፣ ከድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን እና ከአለም የጤና ድርጅት የተውጣጡ ባለሞያዎች የጋራ የክትትል ቡድን በሟቋቋም እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

ሩዋንዳም ከኮንጎ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የኢቦላ መመርመሪያ ጣቢያ በማቋቋም የቁጥጥር ስራ ጀምራለች፡፡

ሩዋንዳ በኮንጎ የተቀሰቀሰውን ወረርሽኝ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን እንዲሁም የአገሯን ዜጎች ከኢቦላ ለመጠበቅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኗን የሩዋንዳው የጤና ጥበቃ ሚስትር ቃል አቀባይ ማሊክ ካዩምባ አስታውቀዋል፡፡

በኮንጎ ሰሜን ምስራቅ ክፍል የተቀሰቀሰው ኢቦላ ወደሌሎች አካባቢዎች የመዛመቱ ጉዳይ እንብዛም ቢሆንም ሁሉም አፍሪካውያን ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባም ነው ቃላቀባዩ ጨምረው የገለፁት፡፡

ምንጭ፡- ዘ ኢስት አፍሪካን