ኬንያ በዚህ ወር ነዳጅ ለመላክ ተዘጋጅታለች

ግንቦት 09፣2009

ኬንያ በዚህ ወር መጨረሻ ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ ተዘጋጅታለች፡፡

ዘኢስት አፍሪካን የተሰኘው የኬንያ ድረ ገፅ እንደዘገበው በሰሜናዊ ኬንያ ቱርካና  ጥልቅ የነዳጅ ጉድጓዶች ተቆፍሮ  የተገኘው ነዳጅ ወደ ሞምባሳ እንደሚያመላልስ

የእንግሊዙ ቱሎው የተሰኘው ነዳጅ አውጪና አመላላሽ ድርጅት ከኬንያ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

በዚህም ድፍድፍ ነዳጅ አመላላሽ መኪኖቹን  ዝግጁ አድርጎ እየጠበቀ መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

የድፍድፍ ነዳጁን ለማመላለስ ሶስት ኩባንያዎች መመረጣቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ ፤ ዘኢስት አፍሪካን