በመካከለኛው አፍሪካ በተቀሰቀሰ አመጽ አንድ መቶ ሰዎች ማገደላቸውን ተመድ አስታወቀ

ግንቦት 09፣2009

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለፈው ሳምንት በተቀሰቀሰ አመጽ ስድስት የመንግስታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪዎችን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። 

የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር አመጹ  በጣም እንዳሳሰበው አስታውቃል።

አመጹ ዋና ከተማዋ ባንግዊን ጨምሮ በትላልቅ ከተሞችና  በአንዳንድ የገጠር አከባቢዎችም እየተስፋፋ መሆኑን ገልጿል።

በደቡብ ምስራቃዊ የባንጋሱ ከተማ በመንግስታቱ ድርጅት ይዞታ አቅራቢያ አንድ መቶ ሰዎች መጠልያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ  አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ቃል አቀባይ ገልጸዋል።

ለሶስት ቀናት በተካሄደው አመጽ አንድ መቶ ሰዎችን ለህልፈት 8 ሺህ 5 መቶ ያህሉ ከቃያቸው አፈናቅሏል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የታጣቂዎች ግጭት ወዳገረሸባት ማእከላዊ አፍሪካ የዲያመንድ መውጫ ከተማ ባንጋሱ ተጨማሪ  የሰላም አስከባሪ ሀይል ለመላክ ማቀዱን አስታውቋል።

ተጨማሪ የሰላም አስከባሪ ሀይሉ ሰላማዊ ዜጎችን መጠበቅ፣ አስፈላጊ የሆኑ የሰብአዊ አቅርቦቶች ለህዝቡ ያደርሳል ተብሏል። ግጭቱን ተከትሎ በከተማዋ የሚኖሩ 35 ሺህ ነዋሪዎች ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸውም ድርጅቱ ገልጿል።

ምንጭ፣አልጀዚራና ብሉምበርግ