ቱርክና አሜሪካ ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብና ለማሻሻል ቃል ገቡ

ግንቦት 9፣ 2009

ቱርክና አሜሪካ ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብና ለማሻሻል ቃል ገቡ፡፡ 

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ከአሜሪካኑ አቻቸው ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራምፕ  ጋር በሁለቱ አገራት ግንኙነት ላይ በኋይት ሃውስ መክረዋል፡፡

ሁላቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብ በሚያስችሉዋቸው ጉዳዮች ትኩረታቸው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራንፕ የቱርክን ህዝብና መንግስት ለበርካታ አመታት ወዳጅ እንደሆነ በመግለፅ፣ ቱርክ ያቀጠናው ስጋት ከሆነው የአይ ኤስ እና ፒኬኬ ከተሰኙንዐው  የኩርድ አማፂያን ጋር የምታደርገውን ውግያ እንደምትገግፍ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህን ቢሉም አሜሪካ በሶሪያ ለሚገኙ ኩርዶች በምታደርገው ድጋፍ ምክንያት በሁለቱ አገራት መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩ ይታወቃል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ግንኙነታቸውን  ለማደስ ቃል ቢገቡም ዳሩ፣ አሜሪካ ዋይፒጂ የተሰኘውን ፀረ አይ ኤስ ቡድን ይዋጋልኛል በሚል ከባድ መሳዎችን ጭምር ማስታጠቋ በመካከላቸው ያሉ ቅሬታዎች ናቸው ተብሏል፡፡    

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ከፕሬዝዳት ትራንፕ ጋር ከመገናኘታቸው ቀደም ብሎ የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር ቢናሊ ይልዲሪም ለፓርቲያቸው ባደረጉት ንግግር አሜሪካ ለሶሪያ ኩርዶች የምታደርገው ድጋፍ በቱርክ ዘንድ ተቀባይነት የለውም  ማለታቸውንም  ሽንዋ ዘግቧል፡፡

ቱርክና አሜሪካ አይ አይኤስን በመዋጋት ሂደት በትብር እየሰሩ ያሉ አገራት ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ሺንዋ