ዶልፊኖች ልክ እንደ ሰው መናገር እንደሚችሉ አንድ ጥናት አመለከተ

ግንቦት 8፣ 2009

ዶልፊኖች በጣም የበለፀገ የንግግር ቋንቋ እንዳላቸውና ይህም ከሰው ልጆች የመግባቢያ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ሳይንቲስቶች ገለጹ᎓᎓

ዶልፊኖች ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ ብቃት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም የሚታወቅ እንደሆነና ባንድ ላይ የተሰባሰቡ ዶልፊኖች በቀላሉ እንደሚግባቡና በየግላቸው የሚያደርጉት መግባባት ግን በሳይንቲስቶች እንዳልተደረሰበት ነው ጥናቱ ያመለከተው᎓᎓

አጥኝዎች እንደሚገልፁት ከሆነ የዶልፊኖች የደም ስር ትርታ መቃጨል እና ፉጨት እስከ አምስት ቃላት መፍጠር እንደሚያስችላቸውና  ሌላ መልስ ከመምጣቱ በፊት ይህ የቃላት ድምፅ  እንደተሰማ ሳይንቲስቶቹ ማረጋገጥ ችለዋል᎓᎓

የቃላት ልውውጡ ልክ በሁለት ሰዎች መካከል ከሚካሄድ የቀላት ልውውጥ ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን የጥናቱ መሪ ዶክተር ያችስላቭ ሪያቦቭ ገልጸዋል᎓᎓

ዶክተሩ እንደሚሉት በዶልፊኖች መካከል የሚፈጠረው ትርታ በሰአት በመጠንና በሚለቀቅበት ድግግሞሽ  አንዱ ከአንዱ ይለያል᎓᎓

ከዚህ ተነስተን እያንዳንዱ ትርታ በዶልፊን የንግግር ቋንቋ  መሰረት አንድ ክስተትን ወይም አንድ ቃልን መወከል እንደሚችል መገመት እንደሚቻል የምርምር ቡድኑ መሪ ገልጸዋል᎓᎓

ምንጭ፤ ዘ ኢንዲፔንደንት