ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራምፕ ሚስጥራዊ መረጃ ለሩሲያ አቃብለዋል ተባለ

ግንቦት 8፣ 2009

የአሜሪካኑ ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራንፕ ስለ አይ ኤስ ከፍተኛ ሚስጥራዊ መረጃ ለሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እንዳቀበሉ የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

መረጃው አውሮፕላኖች ላይ ጥቅም ላይ ስለሚውሉ ላፕቶፖች እንደሆነም ዋሽንግተን ፖስት በዘገባው አስታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራንፕ ለውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ሚስጥራዊ የተባለውን መረጃ የሰጧቸው ባለፈው ሳምንት በነበራቸው ላይ ነው ተብሏል፡፡

የአገር ውስጥ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ማክማስተር የወጣውን ዘገባ ሀሰት ነው ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

የትራንፕ የምርጫ ዘመቻ ከሞኮ ጋር በተያያዘ በርካታ ክሶች በመጣራት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ግን የቀረቡበትን ክሶች በሙሉ ሀሰተኛ ዘገባዎ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ፕሬዝዳት ትራንፕ የምርጫ ተፎካካሪያቸው የነበሩት ሄላሪ ክሊንተንን በሚስጥራዊ መረጃ አያያዛቸው በርካታ ጊዜ ሲወቅሷቸው ቆይተዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ