አዲስ አበባ ዩኒቨሪስቲ ከጄኔራል ኤሌክትሪክስ ጋር አቅም ግንባታ ስምምነት ተፈራረመ

ግንቦት 08፣2009

የአዲስ አበባ ዩኒቨሪስቲ ከጄኔራል ኤሌክትሪክ ጋር በታዳሽ ሃይል ቴክኖሎጂውን የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ስምምነቶችን ተፈራረሙ᎓᎓

ጄኔራል ኤሌክትሪክ ተቋምና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2016 መግቢያ ጀምሮ በጋራ አብረው እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል᎓᎓

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክህሎትን የሚያሳድጉ ስልጠናዎችን ለመስጠት የሚያስችሉ ዕቅዶችን ነድፈው በመተግበር ላይ ይገኛሉ᎓᎓

የጄኔራል ኤሌክትሪክ ተቋም ኢትዮዽያ በእድገትና በትራንስፎርሜሽን እቅድ ትኩረት የሰጠቻቸውን የሃይድሮ ፓዎር ፕሮጀክቶችን በምትሰራበት ወቅት ከፍተኛ እገዛ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ተገልጿል᎓᎓

በተለይ አሌክትሪክን ከነፋስ ከውሃና ከፀሃይ እንድታገኝ ከኢትዮዽያ ኤሌትሪክና ሃይል ተቋም ጋር ተባብሮ እየሰራ ነው᎓᎓

የአዲስ አበባ ኢንጂነሪንግ ኢንስቲቲዩት በአገራችን ግንባር ቀደም ተቋም ሲሆን በ7 የተለያዩ የኢንጂነሪንግ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ በ35 ዘርፎች የማስትሬትና የዶክትሬተ ዲግሪ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል᎓᎓

ምንጭ፤ ዲጂታል ኢንዱስትሪያል