የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት በአፍሪካና በቻይና መካከል ላለው ትብብር ወሳኝ ነው-ሺ ጂንፒንግ

ግንቦት 08፣2009

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ቻይናና ኢትዮጵያ በትብብር ለመስራት የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቱ መጠናከር  እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ  ቻይና ከአፍሪካ ጋር ያላትን  ትብብር  ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ኢትዮጵያ  ለቻይና ወሳኝ  እንደሆነች ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቤጂንግ የተካሄደው ቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም  በተሳተፉበት ወቅት ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሁለቱ አገራት በማምራት አቅም፣ በንግድና ኢኮኖሚ፤ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና በአቨዬሽን ያለውን ትብብር መጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ቻይና በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢንዱስትሪ እና በመሰረት ልማት ግንባታዎች ያላቸው ትብብር  የተሸለ ውጤት ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፤ አፍሪካን ኒውስ