ቻይና ያለገደብ የሚታደርገው የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ታዳጊ አገራትን እየጠቀመ ነው-ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም

ግንቦት 6፣2009

የአለምን ዋነኛ ተግዳሮት ለማቃለል በዕኩልነትና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የአገራት ትስስር እንዲጠናከር ቻይና ጥሪ አቀረበች፡፡

ቻይና የአፍሪካና የኢሲያና የአውሮፓ አገራትን በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር ይፋ ያደረገችው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም በቤጂንግ ተጀምሯል፡፡

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጥንት የአገራትን የንግድ መስመር መነሻ በማድረግ የተጠነሰሰው መርሃ ግብር የአለም አገራትን ህዝቦችን በተለይ ታዳጊ አገራትን በጋራ ተጠቃሚነት የዕድገት ጉዞዋቸውን ለማፋጠን ትልቅ አቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ቻይና ለዚህ ቁርጠኛ አቋም በመያዝ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነች መሆኗን ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል፡፡

ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቻይና ያለገደብ የሚታደርገውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህ የታዳጊ አገራትን ማነቆ ለመፍታት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያም ለአላማው ተፈጻሚነት የበኩሏን ድርሻ እንደምትወጣም ተናግረዋል፡፡

በቤጂንግ በተጀመረው በቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ ከ100 በላይ አገራት የተወጣጡ መሪዎች የከፍተኛ ባለስጣናትና እንዲሁም የተቋማት መሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል፡፡