በመላው ዓለም ያሉ ኮምፒውተሮች ላይ አደጋ ማንዛበቡ ተገለጸ

ግንቦት 5፣ 2009

በአሜሪካ ብሄራዊ የደህንነት ኤጀንሲ የተሰራ ነው በተባለለት የመረጃ ቀበኛ መሳሪያ ምክንያት በመላው ዓለም ያሉ ኮምፒውተሮች ላይ አደጋ ማንዣበቡ ተገለጸ፡፡

በዚህ ምክንያት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኮምፒውተሮች የተዘጉ ሲሆን ይህንን ለማስከፈትም ጠላፊዎቹ እስከ 300 የአሜሪካ ዶላር እየጠየቁ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ወር ዘ ሻዶው ብሮከርስ የተባለ ተቋም የደህንነት መሳሪያዎቹን ከኤጀንሲው መስረቁን ገልጾ ወዲያውም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ማይክሮሶፍት ችግሩን የሚከላከል ሶፍት ዌር ይፋ ቢያደርግም ብዙዎች አልተጠቀሙበትም ብሏል ቢቢሲ በዘገባው፡፡

እስካሁን ድረስ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ስፔንና ጣሊያንን ጨምሮ ችግሩ በ99 አገራት ተከስቷል፡፡