ተከስቶ የነበረው የኤሌክትሪክ አደጋ ስጋት በሳምንቱ መጨረሻ ይፈታል

ግንቦት 4፣2009

በየካ ክፍለ ከተማ የካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤት በሚገኝ አንድ ህንፃ አጠገብ ተቆፍሮ በአግባቡ ካልተደፈነ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ጉድጓድ ውስጥ በየጊዜው የሚሰማ የፍንዳታ ድምፅ ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረባቸው መሆኑን የአከባቢው ነዋሪዎች ለኢቢሲ ገልጸው ነበር፡፡

እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ፤ በአካባቢው ለኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ተብሎ በተቆፈረ ቦታ ላይ የፍንዳታ ድምጽ ይሰማል፤ ድምጹን ተከትሎም የእሳትና የጭስ ምልክት እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ገብረእግዚአብሔር ታፈረ ችግሩ መኖሩን አምነው አሁን የችግሩ ምንነት የተለየ በመሆኑ ችግሩ በአስቸኳይ እንደሚፈታ አረጋግጠዋል፡፡

ቦታው በመተላለፊያ መንገድ ላይ መሆኑና በአጠገቡ ሕፃናትም የሚያልፉበት በመሆኑን ተገልጿል፡፡

ችግሩ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ እንደሚፈታ አቶ ገብረእግዚአብሔር አረጋግጠዋል፡፡

በአብዱልዚዝ ዩሱፍ