አፍሪካውያን ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓታቸውን ሊያጐለብቱ እንደሚገባ ተገለጸ

ግንቦት 04፣ 2009

አፍሪካውያን ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓታቸውን ሊያጐለብቱ እንደሚገባ በመቐለ እየተካሄደ ያለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ አመለከተ፡፡

በመቐለ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ አለምአቀፍ ኮንፈረንስ ላይ የአፍሪካውያን ግጭቶች እንዴት አፍሪካውያን እልባት ማግኘት አለባቸው በሚለው ዙሪያ ብዙ ጥናቶች ቀርበዋል᎓᎓

የችግሩ መነሻም ምንድን ነው  መፍትሄውስ  ምን መሆን አለበት የሚሉ ጥናቶች ቀርበው ብዙ ውይይት ተደርጎባቸዋል᎓᎓

አፍሪካውያን ከዚህ ቀደም ከብዙ አመታት በፊት የተጠቀሙበት ባህላዊ የግጭት አፈታትስ አማራጭ ሳይሆን  እንዴት ነው በዋናነት ከዘመናዊው ጋር በማቀናጀት እንዴት ነው መጠቀም የሚቻለው በሚለው ላይም ብዙ ሃሳቦች ተነስተዋል᎓᎓

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የስነህዝብ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ክንፈ አብርሃ ኮንፈረንሱ ሲታሰብ አፍሪካውያን ባጠቃላይ ያሉባቸውን ችግሮች በተለይ ግጭቶችን በተመለከተ የሚፈቱበት የራሳቸው መንገድ የሆነ ለሺዎች አመታት የተጠቀሙበት ዘይቤ እንዳላቸው ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮንፈረንሱ በሁለት ቀናት ውሎው ወደ 25 የሚጠጉ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል᎓᎓

ሪፖርተር:- ዩሐንስ ፍስሃ