በሳዊዲ አረቢያ የእፎታ ጊዜው የሚመለከታቸውን ኢትዮጵዊያን የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏ ል ፥ ውጭጉዳይ

ግንቦት  03፣ 2009

የታወጀውን የ9ዐ ቀን እፎይታ ጊዜን አስመልክቶ በሳውዲ ያለፈቃድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ለማስመለስ የሚደረገው ጥረት ይበልጥ መጠናከሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ሳምንታዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን  ያለ እንግልት እንዲመለሱ በኢትዮጵያም ይሁን በሳውድ አረቢያ የሚደረገው ጥረት ቀጥሏል ᎓᎓

ቃል አቀባዩ  እንዳሉት የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሳዊዲ አረቢያ ሙሉ ትኩረቱን አድርጎ  ተመላሾቹ ለማስመለስ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል።  

ቀነ ገደቡ ከመድረሱ አስቀድሞ ዜጎች እንዲመለሱና ካለቀ በኋላ  ሊገጥሙ የሚችሉትን ጉዳቶች ለመቀነስ በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቸ ቤተሰቦቻቸውና የሚመለከታቸው አካላት ጥረት ሊጠናከር ይገባዋል ብለዋል።

መንግስት  ከመንግስት ጥረት  ባሻገር መገናኛ ብዙሃን፣  የሃይማኖት ተቋማት፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉ አካላትና  የፖለቲካ ፓርቲዎችም  በዚሁ ብሄራዊ ዘመቻ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ  ጥሪ አርበዋል

የሳውዲ መንግስት የ90 ቀን  እፎይታውን ይፋ ያደረገው መጋቢት 21 ቀን ሲሆን ግማሹ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል᎓᎓

በሌላ ዜና  ኢትዮዽያ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ከሆነች 4 ወር ማሳለፏን የገለፁት ቃል አቀባዩ በነዚህም ጊዜያት አገሪቱ ባገራዊ በአህጉራዊና በአለም አቀፋዊ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ጠንክራ ስትሰራ ቆይታለች ብለዋል᎓᎓

ሪፖርተር ፥ ዳዊት ጣሰው