ኢትዮጵያ ብሪታኒያ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መከሩ

መጋቢት 07 ፣2009

ኢትዮጵያ ከብሪታኒያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሠሰን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ሙባክ ሙሃመድ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያና ብሪታኒያ መካከል በተለያዩ መስኮች ያለው አጋርነት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ገልፀዋል፡፡

የብሪታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰስ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ካለችው ልማት በተጓዳኝ በአፍሪካም ሆነ በምስራቅ አፍሪካ ለሰላምና ፀጥታ መከበር እየተጫወተች ያለው ሚና የሚደንቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የብሪታኒያ አቻቸውን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ብሩክ ተስፋዬ