ድርቅ አፍሪካን ለከፍተኛ የምግብ ዋጋ ጭማሪ እያጋለጣት ነው

በአከባቢው የተከሰተው ድርቅ አገራት ለምግብ የሚያወጡት ወጨ ከፍ ማድረጉን የአለም ምግብ ድርጅት (FAO) ገለጸ፡፡

በየአከባቢው የተከሰተው ድርቅ አገራት የምግብ እህል ከአገራቸው እንዳይወጣ የተለያዩ መንገዶችን መጠቀማቸውን ተከትሎ የምግብ ነክ ሸቀጦች እንዲንሩ ምክንያት መሆኑን የአለም ምግብ ድርጅት ፋኦ ኢኮኖሚስት ጆናታን ፓውንድ ገልጸዋል፡፡

ኬንያ የምግብ እህሎች ከአገሯ እንዳይወጡ ያገደች ሲሆን፤ ዚምባቡዌ ወደ ውጭ በሚወጡ ምግብ ነክ ሸቀጦች ከፍተኛ ታክስ መጣሏን የአለም ምግብ ድርጅት ኢኮኖሚስት ተናግረዋል፡፡

በዚህ ምክንያት ድርቅ የተከሰተባቸው አገራት ምግብ ነክ ሸቀጦችን የሚገዙበት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገልጿል᎓᎓

ምንጭ፤ የጀርመን ድምጽ