ተቋማቱ በቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ ተጎጅዎች የ1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

መጋቢት 07፡2009

ተቋማቱ በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር የመደርመስ አደጋ ለደረሰባቸው  ተጎጅዎች የ1.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

በአዲስ አበባ የደረቅ ቆሻሻ ክምር መደርመስ   ባደረሰው አዳጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍ ኢትዮ- ቴሌኮም የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን  ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልክተቷል፡፡፡፡

ተቋሙ በቀጣይም ተጎጅዎችን በቋሚነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

ድጋፉን ያደረገው ሁሉም አካላት በድጋፉ እንዲሳተፉ ጥሪ መቅረቡን ተከትሎ መሆኑን  ተቋሙ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጉዳት የደረሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎችን በሌላ አካባቢ ለማስፈር እየተደረገ ባለው ጥረት ግምቱ ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ስራ በነፃ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ  የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን  ለተጎጂ በተሰቦች የ324 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የተጎጂ ቤተሰብ 4 ህፃናትንም ለማስተማር ቃል ገብተዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤትና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እያንዳንዳቸው ለተጎጂዎች የሚውል የ100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡