በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር መደርመስ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መንግስት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ

መጋቢት 07፣2009

በአዲስ አበባ በቆሻሻ ክምር መደርመስ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች መንግስት እያደረገ ያለውን  ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 18ኛው መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ  እንዳሉት በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መጋቢት 02፣ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ በደረሰው የቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

በአደጋው  ለጠፋው ህይወትና ንብረት ውድመት መንግስት ማዘኑን በመጥቀስ ቤተሰቦቻቸውንና ንብረታውን በአደጋው ላጡ ወገኖች  አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ለተጎጂ ቤተሰቦችም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

እስከትላንት ምሽት በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ዜጎች ቁጥር 113 መድረሱ መዘገባችን ይታወቃል፡፡

በሰዒድ አለሙ