ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያለፉት ስድስት ወራት የመንግስታቸውን የስራ አፈፃፀም ለፓርላማው እያቀረቡ ነው

መጋቢት 07፣2009

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያለፉት ስድስት ወራት የመንግስታቸውን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት  ለፓርላማው እያቀረቡ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ  ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  የሚያቀርቡት የመንግስታቸውን የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም በአገሪቱ የተከናወኑ ኢኪኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን  በሪፖርታቸው ይዳስሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተለይም አገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱ ያለበትን ደረጃ፣ድርቁን ለመቋቋም በተወሰዱ እርመጃዎች የተሰሩ ስራዎችና ሌሎች አገሪቱ  እየፈፀመቻቸው ያሉ ስራዎች ትኩረት የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሚያቀርቡት ሪፖርት በተጨማሪ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች  ምላሽ የሚሰጡ ይሆናል፡፡

የጠቅላይ ለምክር ቤቱ የሚያቀርቡት ሪፖርት በኢቢሲ በቀጥታ ስርጭት በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡

http://www.ebc.et/web/guest/live-tv