በሶማሊያ ከአልሸባብ አመራሮች አንዱ የሆነው ሁሴን ሳላህ ሙክታር ለሀገሪቱ ጦር እጁን ሰጠ

መጋቢት 01 ፣ 2009

በሶማሊያ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አመራር አንዱ የሆነው ሁሴን ሳላህ ሙክታር ለሀገሪቱ ጦር እጁን መስጠቱና በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል አሚሶም አስታወቀ፡፡

አሚሶምና አዲሱ ተመራጭየሶማያ ፕሬዝዳንት  በቅርቡ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት አዲሲቷን ሶማሊያን በመገንባት ሂደት ውስጥ ትጥቃቸውን በመፍታትእና ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ነበር፡፡

የአመራር አባሉ ሁሴን ሳላህ ሙክታር እጅ መስጠቱም የዚሁ ጥሪ መላሽ እንደሆነ አሚሶምን ጠቅሶ  የኬንያው  ስታንዳርድ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡