በርካታ ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ እስፔን ለመግባት ሲሞክሩ ጉዳት ደረሰባቸው

የካቲት 10፣2009

በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ እስፔን ለመግባት ሲሞክሩ ጉዳት ደረሰባቸው፡፡

ስደተኞቹ ጉዳት የደረሰባቸው በሰሜን አፍሪካ የሚገኘውን የስፔን ግዛት እና ሞሮኮን ለመከለል የታጠረውን 6 ሜትር ከፍታ ያለውን አጥር ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ ነው፡፡

የደህንነት ካሜራዎች እንዳሳዩት 6ዐዐ የሚጠጉ ስደተኞች ናቸው ድንበሩን ጥሰው ለመግባት የሞከሩት፡፡

ቀይ መስቀል ጉዳት ለደረሰባቸው 4ዐዐ የሚሆኑ ስደተኞች ህክምና እያደረገ ነው፡፡

ስደተኞቹ ድንበሩን ጥሰው ለመግባት ሲሞክሩ በስፍራው በጥበቃ ላይ የነበሩ 3 ፖሊሶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በሰሜን አፍሪካ የሚገኙት ሴውታ እና ሜሊላ የተባሉት የስፔን ግዛቶች አውሮፓን ከአፍሪካ ጋር በምድር የሚያገናኙ ብቸኛ ስፍራዎች ናቸው፡፡

በመሆኑም ይህንን አካባቢ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት እንደሚመርጡት የዘበው ቢቢሲ ነው።