የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ የስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን መደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ

የካቲት 10፣2009

በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን በሚፈልገው ደረጃ ለማሳደግ የስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን መደገፍ እንደሚገባ የኮንስትራክሽን ሚንስትሯ ኢንጀነር አይሻ መሀመድ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማህበር 25ኛው የብርእዩቤልዩ በዓሉን አክብሯል።

ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ባሉት አመታት በአማካይ ሀያ ስምንት በመቶ አድጋል።

የዘርፉ አገራዊ ምጣኔ ሀብት ድርሻም 8.5 በመቶ ደርሷል።

ይሁን እንጂ በዘርፉ የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዘርፉ በተፈለገው ደረጃ ላለማደጉ በምክንያትነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን የኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ገልጸዋል።

ሚንስትሯ በአገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የስራ ተቋራጭ ድርጅቶች አቅም መጎልበት አለበትም ብለዋል።

የማሕበሩ አባላትም ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ ላለማደጉ ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች  መኖራቸውን አንስተዋል።

የማሕበሩ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር አበራ በቀለ በበኩላቸው የስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን አቅም በማጎልበት ለዘርፉ እንቅፋት የሆነው የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ለመፍታት ማሕበሩ የድርሻው ይወጣል ብለዋል።

ሪፖርተር :-ይመር አደም