የቡድን ሃያ ሃገራት በአፍሪካ ድህነትን ለመዋጋት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ሊመክሩ ነው

የካቲት 9 ፣2009

የቡድን ሃያ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ድህነትን ለመዋጋት፣ መንግስታዊ ተቋማትን ለማጠናከርና የአህጉሪቱን እምቅ አቅም መጠቀም በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ሊመክሩ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በጀርመን ቦን ከተማ በሚያካሂዱት ስብሰባ የአፍሪካን ጉዳይ ጨምሮ በሶሪያ፣ ወደ አውሮፓ በህገ ወጥ መንገድ በሚገቡ ስደተኞች ጉዳይ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

የቡድን ሃያ አባል ሀገራትን ተዘዋዋሪ ፕሬዝዳንትነትን የያዙት የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲግማር ጋብርኤል የቡድን ሃያ ሀገራት ያላቸውን ልምድ ለአፍሪካ ሃገራት እንዲያጋሩ በትኩረት እሰራለሁ ብለዋል፡፡

ምንጭ ፥ ሮይተርስ