ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ባለሀብቶች ገለፁ

የካቲት 9፣2009

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለፁ፡፡

ባለሀብቶቹ በቦንድ ግዢ ከ41 ሚሊየን ብር በላይ ለግንባታው ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ለግድቡ ግንባታ የቦንድ ግዥ ለፈጸሙ 105 በውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለኃበቶችና ተቋማት የእውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።

እውቅናው የተሰጠው 30 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ ለፈጸሙ መንግሥታዊ የልማት ድርጅቶችና የግል ባለኃብቶች ነው።

በዘርፉ ተሰማርተው የቦንድ ግዥ ለመፈጸም ቃል ከገቡ 193 ባለሀብቶች 55 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 150 ባለኃብቶች  42 ሚሊዮን ብር ያህል መሰብሰቡን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤትና የውሃ መስኖና ኤሌትሪክ ሚኒስቴር ናቸው እውቅና የሰጡት።

ሪፖርተር ፥ ፋሲካ አያሌው