በቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ሰሚት ሳፋሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ፎቅ ህንፃ ተደረመሰ

የካቲት፣ 7 2009

በአዲስ አበባ  ቦሌ  ክፍለ ከተማ  ወረዳ 10 በተለምዶ ሰሚት ሳፋሪ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  ባለ 3 ፎቅ ህንፃ የመደርመስ አደጋ ደረሰ።

የአይን እማኞች እንደተናገሩት  ህንፃው የተደረመሰው  በዛሬው ዕለት ከማለዳው12 ሰዓት ላይ ነው።

በህንፃው ውስጥ  ጥበቃውና ሁለት  ልጆቻቸው የነበሩ ቢሆንም  ምንም ዓይነት የህይወትም ሆነ  የአካል ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የአካባቢው  ነዋሪዎችና የህግ አስከባሪዎች ገልፀዋል።

ህንፃው ገና ግንባታ  ላይ የነበረ  ሲሆን  እንስከ አንደኛ ፎቅ  ግድግዳ ያለቀለት፣ ሁለተኛ ሶስተኛ ፎቅ ግን ኮለን(ተሸካሚ ምሰሶ) ብቻ የነበረው  መሆኑን ነው ነዋሪዎቹ  የገለፁት።

በዚሁ ክፍለ ከተማና ወረዳ በተመሳሳይ ከዛሬ  10  ወራት በፊት ባለ አራት  ፎቅ  ህንፃ  ተደርምሶ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

ሪፖርተር ፥ ሰዒድ  ሙሐመድ