ሙስና ለመዋጋት ሕብረተሰብ ከክልሉ መንግስትጎን እንዲሰለፍ የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በከር ሻሌ ጠየቁ

የካቲት 05፣  2009

 

በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ የተጋረጠውን ሙስና መዋጋት የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሕብረተሰብ የበኩሉን እንዲወጣ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ/ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በከር ሻሌ ጠየቁ፡፡

በመላው ኦሮሚያ ባሉ ዞኖች ሲካሄድ የነበረው የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ ተጠናቋል፡፡

በምዕራብ ሸዋ ዞንና አምቦ ከተማ ሲካሄድ በነበርው የተሃድሶ  መድረክ ላይ የተገኙ  የህብረተሰብ ክፍሎች  በክልሉና በአካባቢያቸው የተጀመሩ የልማት ስራዎች ወደኃላ መቅረትና የስራ እድል አማራጮች አለመስፋት ቅሬታ እንዳሳድረባቸው ተናግረዋል።

መንግስት ጥያቄያቸውን እንዲመልስላቸውና የአካባቢያቸውን ሰላም፣ ልማትና ዕድገት ለማስቀጠል  ከመንግስት ጋር ተባብረው ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

 መድረኩን የመሩት የኦህዴድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በከር ሻሌ በቀጣይ ውጤታማ ሥራ እንዲሰራ መንግስት፣ ሠራተኛና ሕብረተሰቡ የገቡትን ቃል ወደ ሥራ መተርጎም እንዳለባቸው አስገነዝበዋል፡፡

 

ምንጭ፥  የምዕራብ  ሸዋ መንግስትኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት

ፎቶ_ ፋይል