ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ በመሠረተ-ልማት ለማስተሳሰር ትኩረት ሰጥተዋል :- ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ

የካቲት 03፣2009

ኢትዮጵያን ከሶማሌ ላንድ አስተዳደር በመሠረተ-ልማት ለማስተሳሰር በጋራ እንደሚሠሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሶማሌ ላንድ አስተዳደር  የልኡካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በውይይቱ ላይ  እንዳሉት ኢትዮጵያና የሶማሌ ላንድ አስተዳደር የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ ፣በአቅም ግንባታና በመሰረተ  ልማት ዝርጋታ በጋራ ይሰራል።

የሶማሌላንድ አስተዳደር ተማሪዎች በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርታቸውን  እንዲከታተሉ ኢትዮጵያ ትፈቅዳለች ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

የበርበራ ወደብን ተጨማሪ የወደብ አማራጭ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ  ላይ ውይይት መደረጉን የትራስፖርት ሚንስትሩ አቶ  አህመድ ሺዴ ተናግረዋል።

የሶማሌላንድ አስተዳደር የውጭ  ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር  ሰዒድ  ዓሊ  ሺዴ  በበኩላቸው  በኢኮኖሚና በፀጥታ ጉዳዮች በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ  ተናግረዋል።

በተለይም ሶማሌ ላንድ በቂ  የኃይል አቅርቦት ለማግኘት የኢትዮጵያን ልምድ  ትወስዳለች ብለዋል።   

ሪፖርተር ፥ አማረ ተመስገን