በኢትዮጵያ የሚሰማሩ የቱርክ ባለሃብቶችን መንግስት እንደሚደግፋቸው ፕ/ት ሙላቱ አስታወቁ

የካቲት 03፣2009

በኢትዮጵያ መዋዕለንዋያቸውን ለማፍሰስ  ለሚፈለጉ የቱርክ ባለሃብቶች መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በቱርክ ጉብኝታቸው በሃገሪቱ ካሉ ከፍተኛ ባለሃብቶች ጋር በኢስታንቡል ተወያይተዋል፡፡

ቱርክና  ኢትዮጵያ የተለያዩ የንግድ ስራዎችን በጋራ መስራት የሚያስችል ግንኙነት መዘርጋቱን የገለፁት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ፣አሁን ላይ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከአጋርነት ወድ ትብብር መሸጋገሩን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

በመሆኑም ከጨርቃጨርቅ እስከ እስከ እስከ  መሰረት ልማት ባሉት አማራጮች ባለሀብቶቹ  በኢትዮጵያ እንዲሰማሩ ጠይቀዋል።

በተለይም ኢትዮጵያ  በነደፈችው የአረንጋዴ  ኢኮኖሚ ዘርፍ  እንደ ኃይል ማመንጫ ባሉ   አመራጮች ላይ ባለሀብቶቹ  እንዲሰማሩም ፕሬዝዳንት ሙላቱ  ጠይቀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ባለሀብቶች በበኩላቸው  በኢትዮጵያ በተለይም በፓስታና መኮረኒ እንዲሁም በአበባ እርሻና በሌሎችም ዘርፎች  የመሳተፍ ፍላጎት ስላላቸው የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ ከ150 በላይ ባለሀብቶች  በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው 30 ሺህ ለሚሆኑ ኢትዮጵዊያን የስራ ዕድል ፈጥረዋል።

ቱርክ በአፍሪካ ካላት የውጭ ቀጥተኛ  ኢንቨስትመንት ግማሽ ያህሉ በኢትዮጵያ  ነው የሚገኘው። 

ሪፖርተር ፥  ነቢዩ ወንድወሰን