ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጥለውት የነበረው የጉዞ እገዳ እንዲፀናለቸው ያቀረቡት አቤቱታ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ

የካቲት 03፣2009

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ7 አገራት ዜጎች  ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ጥለውት የነበረው የጉዞ እገዳ እንዲፀናለቸው ያቀረቡት አቤቱታ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ።

"9th Us Circuit of Appeals" የተሰኘው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ነው በአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር በኩል የፕሬዝዳንት ትራምፕ የጉዞ ክልከላ  ተግባራዊ  እንዲደረግለት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው።

በተለይም መንግስት በሰባቱ አገራት ዜጎች ላይ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ  የጣለው የጉዞ እገዳ በአገሪቱ ላይ የሽብር ስጋት መኖሩን የሚያረጋግጥ ባለመን፣ሶማሊያ፣ሱዳን፣ሶለመሆኑ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የፈደራል ዳኞች የጉዞ እገዳው እንዳይተገበር የተደረሰው ውሳኔ እንዲከበር አፅንቻለሁ ብሏል።   

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የይግባኝ ሰሚ  ፍርድ ቤቱን ውሳኔ የአሜሪካን ብሄራዊ  ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ  ነው በሚል  በቀጣይ በህግ ለማስከበር እንደሚሟገቱ በትዊተር ገፃቸው ማስታወቃቸውን ቢቢሲ  ዘግቧል።

በውሳኔው መሰረት ወደ  አሜሪካ የጉዞ እገዳ ተጥሎብቸው የነበሩ  የኢራን፣ኢራቅ፣የመን፣ሶማሊያ፣ሱዳን፣ሊቢያና ሶሪያ  ዜጎች በህጋዊ  ቪዛ  ወደ አሜሪካ መግባት ያስችላቸዋል።

ከመላው አለም ወዳ አሜሪካ ተገን በመጠየቅ ለሚገቡ  ስደተኞችም መልካም እፎይታ ያስገኘ  መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

የፍርድ ክርክሩ  ግን ወደ አሜሪካ ከፍተኛውና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እንደሚቀጥል ይጠበቃል።