መከላከያ ሰራዊት ከራሱ አልፎ ለሌሎች ሰላም መከበር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ፕሬዝዳንት ሙላቱ ገለፁ

የካቲት፣ 7 2009

የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ከራሱ አልፎ ለሌሎች አገራት ሰላም መከበር ቁልፍሚና እየተጫወተ መሆኑን ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ገለፁ፡፡

ይህም  የሰራዊቱ  ሚና ኢትዮጵያ ሰላም ወዳድ ስለመሆኗና  ለሰው ልጆች ነፃነት መከበር ያላትን ቁርጠኝነት በጉልህ የሚያሳይ መሆኑን ነው ፕሬዝዳንቱ በጅጅጋ በተከበረው ሀገር አቀፉ የመከላከያ ሰራዊት ቀን የተናገሩት።

አምስተኛው የመከላከያ ሰራዊት  የተከበረው "በህዝባዊ መሰረት የተገነባው ጀግንነታችን እየታደሰ ይኖራል" በሚል መሪ ቃል ነው።

በሰራዊቱ  በሶማሊያ በነበረው ተልዕኮ  ጀብዱ  የፈፀሙ  13ኛው ክፍለ ጦር 4 ሬጅመንት ጀግኖች 2 ደረጃ የሚዳሊያ ሽልማት ከፕሬዝዳንቱ  እጅ ተቀብለዋል፡፡

በበአልሸባብ ጥቃት በመፈጸም ለሶማሊያ ስጋት እየሆነ በመምጣቱ  የመከላከያ ሃይላችን ይህን ሃይል በመደምሰስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን  በበዓሉ ላይ  ፕሬዝዳንቱ  ተናግረዋል።

አምስተኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን  መከበር ወቅቱ  የሚፈልገውን ዘመናዊ  ጦር ለመፍጠር  የተያዘውንሂደት የሚያሳይ  ነው ተብሏል። 

ሪፖርተር፥   ዳዊት ጣሰው