ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት በስፋት እየሳበች መሆኗን ተገለጸ

የካቲት 06፣2009

በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለችው ኢትዮጵያ የውጭ ባለሀብቶችን ቀልብ እየሳበች መሆኗ ተገለጸ።

በአለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ባለፉት አስር አመታት ምጣኔ ሀብቷ ባለሁለት አሃዝ እድገት አሳይቷል።

ኢትዮጵያ የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብዋ ዋነኛው ምክንያት ያላት ማህበራዊና ፖለቲካዊ መረጋጋት፣ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት፣ ጥሩ የአየር ጸባይና ለም መሬት  እንዲሁም የሰለጠነ የሰው ኃይልና ሰፊ የገበያ መዳረሻ  መሆኑን በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ይበልጣል አእምሮ ተናግረዋል።

አቶ አእምሮ የእርሻ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፣ ጨርቃጨርቅ የኤሚካል፣ የመድሀኒትና ብረታብረት ፋብሪካዎች አገሪቱ  ቅድሚያ የምትሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በአገሪቱ እየተገነቡ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የጨርቃጨርቅ፣ ቆዳ፣ መድሀኒት፣ የእርሻ ውጤቶች ማቀነባበሪያ እና የማምረቻ መሳሪያዎች  ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

የኢትዮጵየና የተባበሩት አረብ ኤምሬት የሁለትዮ ሽግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንም አክለዋል።

 ምንጭ:-ግልፍ ቱደይ