ፕ/ት ሙላቱ ተሾመ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ቱርክ ገቡ

ጥር 29፣ 2009

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ቱርክ ገቡ ፡፡

 

ፕሬዝዳንቱ ወደ ቱርክ ያቀኑት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ባደረጉላቸዉ ግብዣ መሰረት ሲሆን  አንካራ ሲደርሱም የሃገሪቱ  የኢኮኖሚ ሚኒስትር ኒሃት ዘይቤክሲ ተቀብለዋቸዋል፡፡

ጉብኝቱ  የሁለቱን አገራት ፖለቲካዊና ኢኮኖማያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ያለመ ነው፡፡

በቱርክና ኢትዮጵያ መካከል 55ዐ ሚሊዮን ዶላር የደረሰውን  የንግድ ልውወጥ  በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያም ዶክተር ሙላቱ ከቱርኩ አቻቸው ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቱርክ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ከቱርክ ኤግዚም ባንክ የምታገኘው ብድር በሚጨምርበት እና የሁለቱ አገራት የባህልና የትምህርት ግንኙነት በሚጠናከርበት ዙሪያ ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቱርክ በኢትዮጵያ ያፈሰሰችው መዋዕለ ንዋይ ከ2 ነጥብ 5 ቢለየን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ካላት ኢንቨስትመንት ግማሹን የሚይዝ ነው፡፡

ሪፖርተር ፥ ነቢዩ ወንድወሰን