አገራት በካንሰር የተያዙ ሰዎችን ህይወት ለማርዘም የሚያስችል አሰራር እንዲተገበሩ ተጠየቀ

ጥር 27፣ 2009

አገራት በካንሰር  የተያዙ  ሰዎችን ህይወት ለማርዘም የሚያስችል አሰራር እንዲተገብሩ የአለም ጤና  ድርጅ ጠየቀ።

ድርጅቱ  ትላንት ይፋ  ባደረገው አዲስ  አቅጣጫ በካንሰር የተያዙ  ሰዎችን የመኖር ዕድል ለማራዘም ህመሙ  ስር  ሳይሰድ ለማከም የሚያስችል የካንሰር ምርምራና ህክምና ማድረግ ላይ ትኩረት እንዲደረግ ጥሪ  አቅርቧል።

በካንሰር በየዓመቱ በተለይም በዝቅተኛና በታዳጊ አገራት  8.8 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚሞቱ  ያመለከተው ድርጅቱ፣ በሽታው ዘግይቶ በመታወቁ  ነው ለብዙዎች ሞት ምክንያት እየሆነ  ያለው ብሏል።

በሽታው በቅድመ ምርመራ መኖሩ  ከተረጋገጠ በህይወት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በህክምና  መከላከል ይቻላል ብሏል መግለጫው።

እናም የአለም ጤና  ድርጅት በየአመቱ በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የአለም  ካንሰር ቀን አስመልክቶ የቅደመ  ካንሰር ምርመራና ህክምና ስርዓት እንዲተገበር የሚያስችል መመሪያ  ይፋ አድርጓል።

ከልብ ህመም ቀጥሎ  ለሞት  ምክንያት  የሆነው ካንሰር በየአመቱ በዓለም ላይ 1.6 ትርሊዮን ዶላር ኪሳራ እያደረሰ  በመሆኑ ትኩረት  እንዲሰጠው ጠይቋል።

በተለይም አገራት የካንሰር  ቅደመ ምርመራን ተግባራዊ  ለማድረግ የሚያስችል  አቅምን እንዲፈጥሩ  ድርጅቱ ጠይቋል።

ምንጭ ፥ የአለም ጤና ጤና ድርጅት