የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል መድሀኒቶችን በተጋነነ ዋጋ እንደሚሸጥ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ገለጹ

ጥር 20፣ 2009

የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል መድሀኒቶችን በተጋነነ ዋጋ እንደሚሸጥ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ገለጹ።

የዳግማዊ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ለህሙማን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ጋር በተገናኘ በሆስፒታሉ የሚሸጡ መድሀኒቶች ዋጋ ውድ መሆን፣ የአቅርቦት ችግር፣ የመድሀኒት መጠን አወሳሰንና ሌሎች ከግዢ ጋር የተያያዙ ችግሮች አገልግሎትን እየተፋተተኑት ናቸው።

በዳግማዊ ሚኒሊክ መድሀኒት ቤት የሚታየው የዋጋ ልዩነት ፒቲዩ በተባለው መድሀኒት ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ናይትሮፍራዞን፣ላታኖፕሮስት፣ ቲኤቲና ቴትራ ሳይክሊን በሚባሉት መድሀኒቶች ዋጋ ላይም የሚታይ ነው።

ሆስፒታሉ በበኩሉ በውድ የተገዙ መድሀኒቶች በመሆናቸው መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሆስፒታሉ የግዥ፣ የመድሀኒትና ሕክምና መሳሪያዎች እያያዝ ላይም ጉድለቶች እንዳሉ ተመልክቷል።

በተለይ ከነማ መድሀኒት ቤትና አንዳንድ የግል መደሀኒት ቤቶች ጋር ሲነጻጸር የተጋነነ የዋጋ ልዩነት መኖሩ ታዝቧል። የሆስፒታሉ መድሃኒት ቤት ከከነማ የመድሃኒት ዋጋ ከፍተኛ በሚባል መልኩ እስከ 560 ብር በአንድ መድሃኒት ላይ ብቻ የዋጋ ጭማሪ አድርጋዋል፡፡

በሌላ በኩልሆ ስፒታሉ መድሀኒት ከመገዛቱ በፊት ብዛቱን በተገቢው መልኩ ለመወሰን የሚያስችሉ አሰራሮችን በትክክል እንደማይጠቀም የመድሀኒት ቤቱ ሰራተኞች ገልጸዋል።

በሆስፒታሉ የሚታየው ሌላ የአሰራር ክፍተት የሕክምና መሳሪያዎችን ሲገዛ ተገቢውን የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ የማያዘጋጅ መሆኑ ነው።

የሕክምና አቅራቢ ድርጅቶች እቃዎችን ሲያስረክቡም ቁጥራቸውን አሳንሰው፣ ቁጥራቸውን ጨምረውና ያላሸነፉባቸውን አይነት የሕክምና እቃዎች ቀላቅለው ሲያመጡ የሚረከብ መሆኑን የፌዴራል ስነ-ምግባር እና ጸረ -ሙስና ኮሚሽን በ2006 ዓ.ም ይፋ ያደረገው ጥናት ያመለክታል።

የዳግማዊ ሪፈራል ሆስፒታል ከዚህ ቀደም ያልነበሩ የህጻናትና የእናቶች ሕክምናን ጨምሮ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶችን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማደረግ እየተንቀሳቀሰ ነው። ይሁን እንጂ ያሉበት የአሰራር ክፍተቶችም በርካታ በመሆናቸው በፍጥነት ሊታረሙ ይገባል።

ሪፖርተር:- ሰይድ መሀመድ