ሳይንትስቶች ለሶስት ገዳይ በሽታዎች ክትባት ለማዘጋጀት እየስሩ መሆናቸውን ገለጹ

ጥር 12፡2009

ሳይንትስቶች ለሶስት ገዳይ በሽታዎች ክትባት ለማዘጋጀት እየሰሩ መሆናቸውን ገለጹ፡፡      

እንደ ሳይንትስቶቹ ገለፀ  በቀጣይ ለአለም ጤና ስጋት የሚሆኑ በሽታዎች  የመተንፈሻ አካል በሽታ (Mers) ፤ አጣዳፍ ትኩሳት( Lassa fever )እና ኢንፌክሽን (Nipah virus) ናቸው፡፡

የመንግስተት ጥምረትና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለእነዚህ ለአለም ጤና ስጋት የሆኑ  በሽታዎችን  ክትባትን ለማፋጠን  460 ሚሊዮን ዶላር ለመደገፍ  ይሁንታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ  የጥምረት መስራች ድርጅቶቹን  ተጨማሪ የ500 ሚሊዮን ዶላር  እንዲፈቅዱ በአለም ኢኮኖሚ  ፎረም  ላይ ጠይቀዋል፡፡

የተላላፊ በሽታ ፈጠራዎች ዝግጁነት  ጥምረት (Cepi) በአምስት አመታት ጊዜ  ውስጥ  በእያንዳጅንዱ በሽታ  ላይ ሁለት  አዳዲስ የሙከራ ክትባቶችን   ለመስራት  እንዳሰቡ ይፋ አድርጓል፡፡

አዳዲስ ክትባቶች  ይፋ ለማድረግ   ረጅም ጊዜና በመቶ ሚሊዮኖች ዶላር  የሚቆጠር ገንዘብ  እንደሚያስፈልግ  ተገልጿል፡፡

በምእራብ አፍሪካ የተከሰተው ኢቦላ በሽታን በመከተል በላቲን አሜሪካ የተከሰተው የዚካ በሽታ አለም  አዳዲስ  ለሚከሰቱ  በሽታች ቅድመ ዝግጅት አለማደረጓን አመላካች  ነው ብለዋል፡፡  

የተላላፊ በሽታ ፈጠራዎች ዝግጁነት  ጥምረት (Cepi) መስራችና  ዳይሬክተር  ጄሬማይ ፈረር  እ.አ.አ. ከ2014  በፊት  ጥቂት የነበረውን የኢቦላ  በሽታ ወረርሽኝ ስርጭት  ለመከላከል  ታማሚዎችን  ከህብረተሰቡ  በማግለል ስርጭቱን ለመቆጣጠር ጥረት ሲደርግ እንደነበር ገለፀዋል፡፡ 

ነገር ግን ይህ ሁኔታ በሰለጠነው አለምና ዝውውር በበዛበት ሁኔታ  የሚከሰቱ  ተላለፊ በሽታዎች  ለመቆጣጠር  በሰፊው መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ