ጠ/ሚ ኃይለማርያም በሳዑዲ አረቢያና በኢትዮጵያ ትብብር ላይ ለመምከር ወደ ሪያድ አቀኑ

ህዳር 11፣2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሳዑዲ አረቢያና በኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ለመምከር ወደ ሪያድ አቀኑ፡፡

             ፎቶ ፥  ፋይል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ለሚኖራቸው ቆይታ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ያለው የንግድ ትስስርና ኢንቨስትመንት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይም ይመክራሉ፡፡

ሁለቱ ሀገራት በምስራቅ አፍሪካ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም በፀረ ሽብር ትብብራቸው ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡

ሪፖርተር፥  ፍትህአወቅ የወንድወሰን