የኢትዮጵያ ቡና በኒውዮርክ ምርጡ ተብሎ ተሸለመ

ህዳር 2፣2009

የኢትዮጵያ ቡና በኒዮርክ  ከተማ  ኢርኔስቶ ኢሊ የተባለ ድርጅት ባዘጋጀው  የዓለም አቀፍ የቡና ሽልማት ስነ ስርዓት የዓመቱ ምርጥ ቡና  ተብሎ ተሸለመ፡፡

ድርጅቱ የሽልማት ስነ ስርዓቱን ሲያዘጋጅ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡

ሽልማቱ የዓለም ምርጥ ቡና አቅራቢዎችን  እውቅና ለመስጠት  መሆኑን አዘጋጁ የጣሊያን ድርጅት አስታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ በተጨማሪም የብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ኢል ሳልቫዶር ፣ ጓቲማላ፣ ሆንድራስ፣ ህንድ እና ኒኳሯንጓ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች መካከል ሶስት ግለሰቦች በሽልማቱ ተካተዋል፡፡

ሽልማቱ ኢትዮጵያ ምርጥ ቡና አቅራቢ መሆኗን የበለጠ የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዘገባው የደይሊ ኮፊ ኒውስ እና የደይሊ ሚል ነው፡፡