የተመራጩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ልጅ ፋሽን ጫማ አቅራቢው ሁጂያን ግሩፕ በኢትዮጵያ በስፋት ሊገባ ነው

ህዳር 01፣2009

የተመራጩ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ ፋሽን ጫማ አቅራቢው ሁጂያን ግሩፕ በኢትዮጵያ  በስፋት  ሊገባ መሆኑን አስታውቋል።

የቻይናው እውቅ የጫማ  አምራች  ሁጂያን ግሩፕ በአዲስ አባባ  የሴቶችን ጫማ ቅርፅ የያዘ  የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመገንባት የሚያችለውን ፕላን አቅርቧል።

የግሩፑ  ዋና  ኃላፊ  ዛንግ ሀሮንግ ለኤ ኤፍ ፒ እንደተናገሩት  በአዲስ አበባ  በሚገነባው የኢንዱስትሪ  ማዕከል በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ብቻ 30 ሺህ ሰራተኞችን የሚሳተፉበት እና  አመታዊ ኢክስፖርት መጠኑ  እስከ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የምርት መጠን ለውጭ ገብያ እንደሚያቀርብ አመልክተዋል።

ሁጂያን ግሩፕ በአሁኑ ጊዜ  የተመራጩ  አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ ልጅ ኢቫንካ ትራንፕ ፋሽን ኮሌኽሽን ከቻይና  እያመረተ የሚያቀርብ ግዙፍ ኩባንያ  ነው።

ሁጂያን ለኢቫንካ ትራምፕ በአመት 100 ሺህ ጥንድ  ጫማዎችን በማቅረብ የአሜሪካ ገበያን በስፋት ተቆጣጥሮታል።

እናም ወደፊት ሁጂያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖረው ተሳትፎ የኢትዮጵያን  ምርት በኢቫንካ በኩል ሰፊ የአሜሪካ ገብያ  እድል ይኖራል ተብሎ ይገመታል ብሏል ዘገባው ።