የህዳሴው ግድብ ግብጽን እንደማይጎዳ ሱዳን ገለፀች

ጥቅምት 03፣2009

ታላቁ  የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ  ግንባታ ግብጽን እንደማይጎዳ ሱዳን ገለፀች።

የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራሂም ጋንዱር ከግብጹ አልሞኒተር  ድረ-ገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ ግብፅ በህዳሴው ግድብ ግንባታ ስጋት ሊገባት አይገባም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በግድቡ ተጠቃሚ ሆኖ ግብፅ እና ሱዳን ሊጎዱበት የሚችል  አሰራር አይኖርም ብለዋል ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሱ፡፡

ኢትዮጵያም ብትሆን ፖለቲካዊ  ማረጋገጫ  መስጠቷን ገልፀዋል።

በመሆኑም ግብጽ ከስጋት መውጣት ይኖርባታል እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፡፡

የሀገራቱ መሪዎች  የግድቡን ተዕጽኖ የሚያጠና ኮሚቴ አቋቁመው ወደ ስራ ማስገባታቸውም ይታወሳል፡፡

የሱዳን መንግስት ግን ከኮሚቴው ሪፖርት በፊት ቀደም ብሎ  የግድቡን መገንባት በአወንታዊነት መቀበሉን ዘገባው ያትታል፡፡

ምንጭ ፥ አልሞኒተር