አሜሪካ አራት የአልሻባብ ታጣቂዎችን ገደለች

መስከረም 18፣ 2009

አሜሪካ ሶማሊያ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አራት የአልሻባብ ታጣቂዎችን  ገደለች፡፡

የአየር ጥቃቱ የተካሄደው የጽንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች ኪሲማዩ ወደብ አቅራቢያ በሶማሊያ ወታደሮችና በአሜሪካ የጦር አማካሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ እንደሆነ አሜሪካ አስታውቃለች፡፡

የሶማሊያ ወታደሮች ከታጣቂዎቹ የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት በመመከት በርካታ የአልሻባብ አባላትን ቢገድሉም የጽንፈኛው ቡድን ጥቃት በመቀጠሉ ሳቢያ አሜሪካ በአየር ጥቃት አራት የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደል ችላለች  ነው የተባለው፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አሜሪካ በአየር ጥቃት በርካታ የቡድኑን መሪዎች በሶማሊያ መግደል እንደቻለች ይታወቃል፡፡

አልሻባብ በደረሰበት ወታደራዊ ጥቃት በሶማሊያ በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ተሸሽጎ ይገኛል፡፡

ምንጭ፦ሲሲቲቪ