የጣሊያን ጠረፍ ጠባቂዎች ከሊቢያ የተነሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን በህይወት ታደጉ

ነሐሴ 24፣2008

የጣሊያን ጠረፍ ጠባቂዎች  ከሊያ የተነሱ  በሺዎች  የሚቆጠሩ ስደተኞችን በህይወት መታደጋቸው አስታወቁ።

ከሊቢያ የጠረፍ ዳርቻ 20 ኪሎ  ሜትር ርቀት ባለ የሜድትራኒያን የባህር ክፍል ላይ የነበሩ ከ6500 በላይ ስደተኞችን በህይወት ማትረፋቸው ጠረፍ ጠባቂዎቹ ተናግረዋል።

ይህ ከ40 ጊዜ  በላይ ምልልስ የፈጀው የህይወት አድን ተልዕኮ በአይነቱ  በትልቅነታቸው ከተመደቡት ውስጥ ተካቷል።   

በህይወት የተረፉት ስደተኞቹ  የኤርትራ እና የሶማሊያ  ዜጎች መሆናቸው ቢቢሲ አመልክቷል።

በተመሳሳይ ከዚህ አደጋ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እሁድ እለትም በተመሳሳይ በዚሁ ቦታ የአንድ ሺ አንድ መቶ ስደተኞች ህይወት መታደግ መቻሉ ተገልጿል።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀው 275 ሺህ የሚሆኑ  ስደተኞች  ከሊያ ለመውጣት  እየተጠባበቁ መሆናቸውን  ቢበሲ ዘግቧል።