Ebc Blog Ebc Blog

መንግስት በመላ አገሪቱ የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት እያደረገ ላለው ጥረት ውጤታማነት ከጉዳዩ ባለቤት ወጣቱ፣ ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ከአጠቃላይ ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ?

Wed Sep 28 06:25:58 GMT 2016


ሃሳብዎን ያካፍሉን ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር አንድ ሶስተኛ ያህሉን የሚሆነው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል አገራችን አሁን ላለችበትም ሆነ የመጪውን ጊዜ ሁለንተናዊ እጣ ፈንታዋን የመወሰን እድልና አቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ወጣቱ አገራችን እየገነባች ያለውን የዴሞክራሲያዊ ስርአት ለማጠናከርና የኢኮኖሚ እድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እያካሄደች ባለው ጥረት ሂደት ላይ ያላትን ትልቅ ስትራቴጂካዊ እድል ለመጠቀምም ሆነ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተደቀኑባትን ፈተናዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመፍታት ወሳኙንና የማይተካውን ሚና የሚጫወተው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ እሙን ነው ፡፡ በመሆኑም መንግስት የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም ለዚህ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ የእድገት ፓኬጆችን ቀርጾ ተግባራዊ ካደረገ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ የፖሊሲና የስትራቴጂውም ሆነ የማስፈጸሚያ ፓኬጁ ዋነኛ አላማም ወጣቶች በኢትዮጵያ እየተገነባ ባለው የዴሞክራሲ ስርአት፣ በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ፣ በኢኮኖሚያዊ ፣ የማህበራዊና የመሳሰሉት መስኮች ዋነኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማስቻል ሲሆን በዚህ ረገድ በአገራችን ባለፉት አመታት የማይናቁ ተግባራት ተከናውነዋል፤ የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለፉት አመታት በተከናወኑ ተግባራትም በመላ አገሪቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ የተለያዩ ዘርፎች በመደራጀት ራሳቸውን እየለወጡ ቢገኙም በአጠቃላይ በአገሪቱ ከሚስተዋለው የስራ አጥነት ችግር ስፋትና መጠን ጋር ሲነጻጸር ግን በዚህ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ገና በጅምር ደረጃ የሚታዩና ብዙ የሚቀራቸው እንደሆኑ መንግስት በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር በበቂ ሁኔታ ለመፍታት መንግስት በቅርቡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ በማዋቀር በ1998 ተግባራዊ የሆነውን የወጣቶች የእድገትና የልማት ፓኬጅ እንደገና በመከለስ ከበፊቱ በላቀ ሁኔታ በስትራቴጂ ደረጃ እንዲቀረጽ መደረጉን በቅርቡ ይፋ አድርጓል ፤ ይህም የስትራቴጂ ጥናት እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከመጪው ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም መንግስት ገልጿል፡፡ መንግስት በመላ አገሪቱ የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት እያደረገ ላለው ይህን መሰል ጥረት ውጤታማነት ከጉዳዩ ባለቤት ወጣቱ፣ ከሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ከአጠቃላይ ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ? ከዚህ የተለየ አስተያየትና የመፍትሄ ሃሳብ አለ የሚሉት ካለም ሃሳብዎን ያለመቆጠብ በነጻነት ያካፍሉን፡፡

ኢህአዴግ እያካሄደ ያለው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከመንግስት ፣ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና በአጠቃላይ ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል?

Fri Sep 23 06:33:22 GMT 2016


ሐሳብዎን ያካፍሉን ኢህአዴግ እያካሄደ ያለው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከመንግስት ፣ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና በአጠቃላይ ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል? በቅርቡ ኢህአዴግ ያለፉትን 15 ዓመታት የተሃድሶ ጉዞን በመገምገም ‹በጥልቀት መታደስ› የሚል አዲስ አቅጣጫን አስቀምጧል፡፡ ከዚህ በመነሳት ድርጅቱ ምንም እንኳን በተሃድሶ መስመር ውስጥ ያለ ቢሆንም እንደገና በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ኢህአዴግ ተግባራዊ እያደረገ ባለው የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር ህዝቦች በአገሪቱ በሚካሄደው ልማት ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፤ይሁን እንጂ በዚህ ሂደት የሚያጋጥሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እንዲቻልም ለመብቱና ለልማቱ ተጠቃሚነት የሚታገል ጠያቂ ማህበረሰብ በመፍጠር ሂደት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል፡፡ ድርጅቱ በዋናነት የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈጥሩ፣ የመንግስት ስልጣንን ያለአግባብ የሚጠቀሙና በድርጅቱ ስም የሚነግዱ ግለሰቦች በውስጡ እንዳሉ በማመን በጥልቀት በመታደስ ከእነዚህ ችግሮች ለመውጣት ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡በዚህ ረገድ ሰሞኑን ኦህዴድ እየወሰደ ያለውን የመታደስ እንቅስቃሴ እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ኢህአዴግ በጥልቀት ለመታደስ የጀመረው እንቅስቃሴ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ከመንግስት ፣ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና በአጠቃላይ ከማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ?

ትምህርት ቤቶች ከፖለቲካና ሃይማኖት ተጽእኖ ነፃ ሆነው የመማርና የማስተማር ተልዕኮአቸውን በብቃት እንዲወጡ ከመምህራን፣ ከተማሪዎችና ከወላጆች ምን ይጠበቃል?

Thu Sep 15 16:22:46 GMT 2016


በተለያዩ ደረጃ ያሉ ት/ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡ የመምህራን ውይይት የትምህርት አሰጣጥ፣ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል፣ ፍትሓዊነት፣ መልካም አስተዳደርና የተማሪዎች ስነ ምግባር ላይ ያተኩራል፡፡ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለው የመምህራን ውይይት ለትምህርት ጥራት መሻሻል፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 90(2) መሰረት ትምህርት ቤቶች ከፖለቲካና ሃይማኖት ተጽእኖ ነፃ ሆነው የመማርና የማስተማር ተልዕኮአቸውን እንዲወጡ ውይይቱ ምን ሚና ይኖረዋል ብለው ያስባሉ? በውይይቱ ላይስ ከመምህራን፣ ከተማሪዎችና ከወላጆች ምን ይጠበቃል? ኢትዮጵያ በስነ ምግባር የታነፀ የተማረ ኃይል በማፍራት አገሪቱ ካደጉትና ከሰለጠኑት አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያለው አስተዋጽኦስ እንዴት ይገልጹታል? በመምህራን ውይይት ላይ ቢካተቱ የሚሏቸው ተጨማሪ ሐሳቦች ይኖር ይሆን? ሐሳብ እንለዋወጥበት

የአሉባልታ መዛመትን ለመቀነስ ከየትኛውም ወገን የሚወጡ መረጃዎችን አመዛዝኖ የመቀበል በህል እንዲዳብርና ግልጽነት በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ እንዲሰርጽ ከማህበረሰቡና ከመንግስት አካላት ምን ይጠበቃል ይላሉ?

Sat Aug 20 14:47:01 GMT 2016


አሉባልታ ማለት በሰዎች መካከል በሚደረገው ተግባቦት ተጨባጭና በቂ ማስረጃ የሌላቸውንና የማይቀርብባቸውን መረጃዎች ይዞ "እንዲህ ተፈጠረ፤እንዲህ ተደረገ" በሚል ሁኔታዎችን በማጋነን አሊያም በማንኳሰስ የሚቀርብበት ነው ፤አሉባልታ ቀድሞም የነበረ ቢሆንም አሁን ባለንበት የ21 ኛው ክፍለ ዘመን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ለኡባልታ መዛመትና ስርጭት ሰፊ አሉታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያዎች ትክክለኛና ገንቢ ለሆነ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የማበርከታቸውን ያህል በተለይም ፌስቡክን የመሰሉ የማህበራዊ ሚዲያ ውጤቶ ጥቂቶች ከእውነታው ያፈነገጠ፣ ሃሰተኛ መረጃዎችንና አሉባልታዎችን በሃሰተኛ ስም(fake name የፌስቡክ አካውንት ከፍተው እያሰራጩ ያሉበትን ሁኔታ አመቻችቷል፤ በተለይ አሁን አሁን ደግሞ ሃሰተኛ መረጃዎችንና አሉባልታዎችን የሚያሰራጩ አንዳንድ አካላት ከግለሰብ አልፎ የአንድን ብሄር ስም አሊያም የአንድን ቋንቋ ተናጋሪዎች ስም በመወከል ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ፣ ትላልቅ ማህበራዊ ቀውስ ሊፈጥሩ የሚችሉ አሉባልታዎችና የሃሰት መረጃዎች ሲለቁ ይስተዋላሉ፤ይህንንም በማድረግ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ለጥፋት አላማቸው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፤ የአሜሪካ ሳይኮሎጂስቶች በቅርቡ ባካሄዱት ጥናት አሁን አሁን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚወጡ አሉባልታዎች የግለሰብ ህይወትን በመጉዳት ብቻ ሳይወሰን የሰዎችን አስተሳሰብ በማበላሸት፣ ለክፉ ነገር በማነሳሳት፣ ከሞራል ያፈነገጠ የአገራዊና የማህበረሰብን ደህንነት የሚጎዱ ተግባራት እንዲፈጸሙም መሳሪያ እየሆኑ ነው ካሉ በሁዋላ በመሆኑም በማህበራዊ ድረገጾች በዘፈቀደ የጋዜጠኝነት ስነ ምግባር የሚጠይቀው የሚዛናዊነት ፣ትክለኛነትና ተጨባጭነት መርህ ሳይጠበቁ በዘፈቀደ በግለሰቦች የሚሰራጩ አሉባልታዎችን በሃሰት የተቀናበሩ መረጃዎችን እንደ እውነተኛ መረጃ ከመቀበል ይልቅ ማህበረሰቡ መረጃዎችን አጣርቶና ተአማኒና በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፉ መሆናቸውን አረጋግጦ ሊቀበል እንደሚገባ ይመክራሉ፤ በመሆኑም የአሉባልታ መዛመትን ለመቀነስ መንግስታዊ አካላትን ጨምሮ ግልጽነት በሁሉም ማህበረሰብ ውሥጥ እንዲሰርጽ በሰዎች መካከል ያለውን የሀሳብ ልዩነት በማክበር ትክክለኛ የሃሳብ ልውውጥ መድረክ እንዲጠናከርና ከየትኛውም ወገን የሚወጡ መረጃዎችን አመዛዝኖ የመቀበል በህል እንዲዳብር ከማህበረሰቡና ከመንግስት አካላት ምን ይጠበቃል ይላሉ ሃሳብዎን ያካፍሉን

የጥላቻ ንግግር የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ?

Thu Aug 11 15:39:25 GMT 2016


የጥላቻ ንግግር የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ? የጥላቻ ንግግር (hate speech) የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በፖለቲካዊ አመለካከት፣በሚከተሉት እምነት ፣በዘር ፣በትምህርት ደረጃ፣ በሃብት ደረጃ በቀለማቸው በአነዚህና ሌሎችም የማንወዳቸውን ሰዎች የምንፈርጅበት ወይም ስብእናቸውን የምንገፍበት ነው፤ ይህ የጥላቻ ንግግር አልፎ ሲሄድም እነዚህን ሰዎች አልወዳቸውምና ስለዚህም ይጥፉ፤ ይወገዱ ፈረንጆቹ (Call for action) የሚሉት ደረጃ የሚደርሰው አደገኛ ንግግር (dangerous speech) የሚባለውም የዚሁ የጥላቻ ንግግር አካል ነው፡፡ ምሁራን የጥላቻ ንግግር ሁልጊዜ ስለተነገረ ብቻ ጉዳት ያደርሳል የሚል ድምዳሜ ባያደርስም ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሆን ተብሎ የሚነገር የጥላቻ ንግግር በመጀመሪያ ደረጃ ኢላማ የተደረገውን አካል ለመፈረጅ፣ በዚህም ሳያበቃ ሰይጣናዊ ምስል እንዲይዝ ማድረግ ቀጥሎ ደግሞ ከምድረገጽ እንዲጠፋ ማነሳሳት አላማን ያነገበ ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም በግለሰቦች ወይም በህዝቦች መካከል አለመግባባት፣ ብሎም ግጭትን ሊቀሰቅስ የሚችሉ የጥላቻና አደገኛ ንግግሮች በፊትም የነበሩ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ለዚህ ሁኔታ መባባስ የማህበራዊ ሚዲያዎች አሉታዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ ማህበራዊ ሚዲያዎች ማህበረሰቡን ለሚጎዱ እንዲህ አይነት መጥፎ ተግባራት ማራመጃ እንዳይውሉ ይልቁንም ለአገር ሰላምና የጋራ መግባባት በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ከሰው አክባሪ ባህላችን ጋር የሚቃረን ይህ የጥላቻ ንግግርን እንዴት መቀነስ ወይም ማስቀረት እንችላለን?በአጠቃላይም የጥላቻ ንግግርን የሚጸየፍ ማህበረሰብን ለመፍጠር ምን መደረግ አለበት ይላሉ? እስቲ እንወያይበት

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ እያስመዘገበች እንዳለችው እምርታ በሌሎች የተለያዩ ዘርፎች አሁን ከለችበት ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ?

Tue Jul 19 11:46:48 GMT 2016


ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ እያስመዘገበች እንዳለችው እምርታ በሌሎች የተለያዩ ዘርፎች አሁን ከለችበት ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ? ኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤትና የዓለም አገራት ጋር በምታደርገው ውጤታማ ዲፕሎማሲ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያገኘች ነው፡፡ በቅርቡም ከ190 ድምጽ 185 ድምጽ በመግኘት የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆናለች፡፡ አገሪቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች ነው፡፡ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቃል አቀባይ በመሆንም በዓለም አቀፍ መድረክ የአፍሪካ ድምጽ እንዲሰማ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጋለች፡፡ እንደ ኦባማ፣ ባን ኪ ሙን፣ ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ፓርክ ጄን ሄይና ሌሎች ታላላቅ የዓለም መሪዎች ኢትዮጵያን በመጎብኘት ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን መስክረዋል፡፡ በመሆኑ እርስዎ የአገሪቱን የዲፕሎማሲ ግንኙነት፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያላት ተሰሚነት መጉላትና ለአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት እንዴት ይገመግሙታል? አገሪቱ እንደ ዲፕሎማሲያዊ ድሏ ሁሉ በተለያዩ ዘርፎች አሁን ከለችበት ይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ? ሐሳብ እንለዋወጥበት

የመከላከያ ሰራዊታችን የአገርን ሰላም፣ልማትና መረጋጋት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ማንኛውንም የሽብርና የጥፋት ሃይል ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ላይ ያለዎትን አስተያየት ቢያካፍሉን?

Thu Jun 16 12:40:34 GMT 2016


የሰላም ዘብ የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአገር ውስጥ ሰላምና መረጋጋትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት በአጎራባች ሶማሊያ የመሸገውን የአልሸባብ የጥፋት ሃይል ጨምሮ የአካባቢውን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሌሎች ጸረ ሰላም ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርቡ አልሸባብ የሰነዘረውን የማጥቃት ሙከራ ካከሸፈ በኋላ የሽብር ኃይሉ ላይ በከፈተው መልሶ የማጥቃት እርምጃ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአልሸባብ ታጣቂዎችን ደምስሷል፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያም ማርኳል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ የኤርትራ ጸረ ሰላም ሃይል በጸረና ግንባር የከፈተውን ትንኮሳ በመመከት የመከላከያ ሰራዊታችን በወሰደው አጸፋዊ እርምጃ የኤርትራ የመከላከያ ኃይል ክፉኛ ተመቷል፡፡ ስለዚህ የመከላከያ ሰራዊታችን የአገርን ሰላም፣ልማትና መረጋጋት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ማንኛውንም የሽብርና የጥፋት ሃይል ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ላይ ያለዎትን አስተያየት ቢያካፍሉን? የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ጸጥታና መረጋጋት በዘላቂነት በማስጠበቅ የአገርን ሰላምና ልማት አስተማማኝ ለማድረግ አካባቢውን በሚያተራምሱ የሽብርና የጥፋት ሃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃስ ምን መምሰል አለበት ይላሉ? ሃሳብዎን ያካፍሉን?

አዲሱንና ሕጋዊውን የውጭ አገራት የስራ ስምሪት እንዴት ያዩታል? ሃሳብዎን ያካፍሉን

Tue Jun 07 11:27:20 GMT 2016


ሐሳብ እንለዋወጥበት በቅርቡ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 32 ድንጋጌ መሰረት ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ወደፈለጉት አገር ሄደው እንዲሰሩ ለማስቻል እንቅስቃስ እያደረገ መሆኑን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት መግለጹ ይታወሳል፡፡ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለመከላከል ሲባል ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ወዳደረጉ አገራት ብቻ እንዲሄዱ ከዚህ በፊት የነበረው የግል ስራና ሰራተኛ ማገናኘት አዋጅ 632/2001 ተሻሽሎ በአዲስ የውጭ አገራት የስራ ስምሪት አዋጅ 923/2008 ተተክቷል፡፡ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ለውጭ አገራት የስራ ስምሪት 8ኛ ክፍልና ከዚያ በላይ መማርና በቤተሰብ አያያዝና እንክብካቤ እንዲሁም ሌሎች ስልጠና መውሰድ ግዴታ ነው ተብሏል፡፡ በህገ ወጥ መንገድ ለሚደረግ ስደት መባባስ የቤተሰብና የጓደኛ ግፊት፤ የሕገ ወጥ ደላሎች በአቋሯጭ የመክበር ፍላጎት፤ ለውጭ አገራት የሚሰጥ የተዛባ አመለካከትና ስነ ምግባር የጎደላቸው ኤጀንሲዎች ለሕገ ወጥ ዝውውር ምክንያት ናቸው ብሏል የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡ በመሆኑም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የወሰደውን ይህን እርምጃ እንዴት ያዩታል? በዚህ ረገድ ቢካተት ጥሩ ነበር የምትሉት የመፍትሄ ሃሳብ ካለ ብትጠቁሙን? የትምህርት ዝግጅትና በቂ ስልጠና ወስደው ለውጭ ስራ ስምሪት መሰማራትንስ እንዴት ያዩታል? እስቲ ሐሳብ እንለዋወጥበት፡፡

አገሪቱ የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል ከመንግስትና ከህዝብ ምን ይጠበቃል? ትምክተኝነትና ጠባብነትን ለመዋጋትስ ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

Fri May 27 12:45:02 GMT 2016


ሐሳብ እንለዋወጥበት አገሪቱ የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል ከመንግስትና ከህዝብ ምን ይጠበቃል? ትምክተኝነትና ጠባብነትን ለመዋጋትስ ምን መደረግ አለበት ይላሉ? የበርካታ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አገር የሆነችው ኢትዮጵያ ባለፉት 25 ዓመታት ብዝሃነት የሚያስተናግድ ስርዓት ከገነባች ወዲህ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎች ተመዝግበዋል፡፡በአገሪቱ እውን የሆነው ህገ መንግስታዊ ስርአት በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እውን እንዲሆን አስችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በአገሪቱ ተግባራዊ የሆነው ፌዴራል ስርአት ላይ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የጠባብነትና ትምክተኝነት አመለካከት ከድህነት ለመውጣትና ለልማት የሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ናቸውና እነዚህን የተሳሳቱ አመለካከቶች ለማስተካከል ምን መደረግ አለበት ይላሉ? ሃሳብዎን ያካፍሉን

ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ሂደት ከመንግስት፣ከሌሎች ባለድርሻ አካላትና ከህብረተሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ?

Fri May 20 13:53:48 GMT 2016


በቅርቡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች መንግስት ከፍተኛ ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግና ስልጠና በመስጠት ለወጣቶች የስራ እድል የመፍጠር እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ መንግስት በሁለተኛው የእድገትና ትራስፎርሜሽን እቅድ ላይ የወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት በአገሪቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሂደት ውስጥ ዋነኛ ተዋናይ እንዲሁም ተጠቃሚ ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በአገሪቱ ውስጥ በስራ ፈጠራ ረገድ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በመንግስት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንዴት ያዩታል? ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ሂደት ከመንግስት፣ ከባለድርሻ አካላትና ከህብረተሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ? በአጠቃላይ ስራ ፈጠራን በተመለከተ ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ይላሉ? ሐሳብ እንለዋወጥበት

በመዲናዋ ባሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከኢትዮጵያዊነት ወግ ያፈነገጡ የተማሪዎችን ሞራልና እሴት የሚጎዱ ተግባራት እንዳይካሄዱ በመከላከል ረገድ ከወላጆች ፣ መምህራንና ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ ፤ ሃሳብ እንለዋወጥበት

Wed May 18 09:52:30 GMT 2016


ሃሳብ እንለዋወጥበት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የሚከበሩ ኢትዮጵያዊ መሠረት የሌላቸው እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ የሚል ስያሜ ያላቸው ቀናቶች የተማሪዎችን አስተሳሰብ እየጎዱ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅቷል፤ በ2009 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ የሚደረገው ይሀው መመሪያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ በሚሆኑበት ወቅት በእያንዳንዱ ትምህርት ቤቶች የሚከበሩ ቀኖች ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶችን ብቻ የሚያጎለብቱ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፤ በመዲናዋ ባሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከኢትዮጵያዊነት ወግ ያፈነገጡ የተማሪዎችን ሞራልና እሴት የሚጎዱ ተግባራት እንዳይካሄዱ በመከላከል ረገድ ከወላጆች ፣ መምህራንና ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ ፤

ሃሳብ እንለዋወጥበት

Wed May 18 09:38:46 GMT 2016


በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የሚከበሩ ኢትዮጵያዊ መሠረት የሌላቸው እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ የሚል ስያሜ ያላቸው ቀናቶች የተማሪዎችን አስተሳሰብ እየጎዱ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅቷል፤ በ2009 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ የሚደረገው ይሀው መመሪያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ በሚሆኑበት ወቅት በእያንዳንዱ ትምህርት ቤቶች የሚከበሩ ቀኖች ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶችን ብቻ የሚያጎለብቱ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፤ በመዲናዋ ባሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከኢትዮጵያዊነት ወግ ያፈነገጡ የተማሪዎችን ሞራልና እሴት የሚጎዱ ተግባራት እንዳይካሄዱ በመከላከል ረገድ ከወላጆች ፣ መምህራንና ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ ፤ ሃሳብ እንለዋወጥበት

ሃሳብ እንለዋወጥበት በኢትዮጵያ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ይላሉ?

Fri Apr 29 08:39:54 GMT 2016


ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ይላሉ? ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አሉ የሚሏቸው ተግዳሮቶችን አንስተን እስቲ ሃሳብ እንለዋወጥበት፡፡ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት በርካታ አንቀጾች የዜጎች ሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቶች እንዲከበሩ ይደነግጋል፡፡ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 መሰረት ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት መያዝ ይችላል፤ ሐሳቡን ገደብ ሳይደረግበት በቃል ወይም በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውም መረጃና ሐሳብ የማሰባሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ተጎናጽፏል፡፡ በዚህ መሰረት በአሁኑ ወቅት ዜጎች ሐሳባቸውን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንና ትዊተርን ጨምሮ በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክን በመጠቀም ሐሳባቸውን በነፃነት እየገለጹ ነው፤ የተለያዩ መረጃዎችንም እየተለዋወጡበት ይገኛሉ፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያ ህገ መንግስታዊ ስርአት ያለ አንዳች ገደብ የተረጋገጠው የዜጎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ይላሉ ፤ በዚህ ረገድ አሉ የሚሏቸው ተግዳሮቶችን አንስተን እስቲ ሃሳብ እንለዋወጥበት ፤ ዜጎች የመሰላቸውን ሐሳብ በእምነት የመያዝና በተለያዩ ሚዲያዎች የማንጸባረቅ ጥቅሙስ ምንድን ነውይላሉ? ይህንን ይበልጥ የማጠናከር ጠቀሜታን እንዴት ይገልጹታል? እንወያይበት፡፡

በወጣቶች የስራ እድልና የስራ ፈጠራ ረገድ የሚታዩ ችግሮች ላይ ሃሳብ እንለዋወጥ?

Wed Apr 13 13:30:22 GMT 2016


ከስራ ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የብድር አቅርቦት፣ የንግድ ፈቃድና የመሳሰሉት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተቸግራችኋል? ለመደራጀትና ብድር ለመጠየቅስ እድሉን አላገኛችሁም? በአገራችን የሚታየውን የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ትላላችሁ? ከማን ምን ይጠበቃል? ሃሳብ እንለዋወጥበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ወጣቱ ኃይል ተደራጅቶ በመስራት እንዲለወጥ የተቻለውን እገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡አንዳንድ ወጣቶችም መንግስት ባመቻቸላቸው እድል ተጠቅመው ሰርተው መለወጣቸውን ይናገራሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ትምህርታቸውን አጠናቀው ስራ ያላገኙ ወጣቶችም አሉ፡፡ በተለያዩ መልኩ ተደራጅተው አቅማቸው በፈቀደው የስራ ፈጠራ መስክ ለመሰማራት ከመንግስት ብድርና ሌሎች ድጋፎችን ከጠየቁ ወጣቶች አንዳንዶቹ ደግሞ በዚህ ረገድ ያሉ ሁኔታዎች የሚጠበቀውን ያህል ምቹ አይደሉም ሲሉ ይደመጣል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት የንግድ ፍቃድ እንኳን ለማውጣት ገንዘብና ሌሎች መደለያዎችን እንደሚጠይቋቸው አሊያም ደግሞ በቀጠሮ እንደሚያመላልሷቸው ይናገራሉ፡፡ ግብር መክፋል የማንም ግዴታ ቢሆንም አንዳንዴ ከገቢያችን ጋር የማይመጣጠን ግብር እንጠየቃለን ሲሉም ያማርራሉ ፡፡ አንዳንዶቹ በዚህና መሰል ምክንያቶች ተስፋ መቁረጥ እያጋጠማቸው እንደሆነ ይገልጻሉና በዚህ ረገድ በተለይ ወጣቶች ምን አጋጠማችሁ? የንግድ ፈቃድ ለማውጣት ተቸግራችኋል? ለመደራጀትና ብድር ለመጠየቅስ እድሉን አላገኛችሁም? በአገራችን የሚታየውን የስራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ትላላችሁ? ከማን ምን ይጠበቃል? ሃሳብ እንለዋወጥበት

የእኛው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለፍጻሜ እስኪደርስ ከመንግስት ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበረሰቡና በአጠቃላይ ከእያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ምን ይጠበቃል ይላሉ ?

Sat Apr 02 15:30:54 GMT 2016


ልክ የዛሬ አምስት አመት መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አሁን ከግማሽ በላይ ተጠናቆ ውሃ መቋጠር ወደ ሚችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ የግድቡ ግንባታ አገሪቱ ሌሎች ታላላቅ ግድቦችና ፕሮጀክቶችን ያለ ማንም እገዛ በራሷ አቅም የመገንባት ብቃት እንዳላት በተግባር ያረጋገጠ ነው ። የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና አገራዊ የምህንድስና አቅምን በማጎልበት ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው ሲሆን አገራችን ከአፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚ ለመገንባት ያላትን ዕቅድ በማሳካት ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ፤ ይህም አገራችን በአፍሪካም ሆነ በአለም ያላትን ተደማጭነት ከማሳደግና አገራችን ቀድሞ የነበራትን ክብር ከመመለስ አንጻር የሚኖረው ፋይዳ የላቀ ነው፡፡ይህ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው የእኛው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለፍጻሜ እስኪደርስ ከመንግስት ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበረሰቡና በአጠቃላይ ከእያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን ዜጎች ምን ይጠበቃል ይላሉ ? እስቲ እንነጋገርበት ፡፡

በፌስቡክ ምን ያህል ተጠቀምን? ምን ያህልስ ተጎዳን?

Fri Apr 01 10:37:41 GMT 2016


ማህበራዊ ሚዲያዎች /ፌስ ቡክ፣ ቲውተር፣ ዩቲውብ፣ ብሎግ፣ ሊንክዲን፣ፍሊከር ወዘተ/ የመሳሰሉት እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ እያደጉና ሰፊ ተቀባይነት እያገኙ የመጡ አዳዲስ ወይም ዘመናዊ ሚዲያዎች ዓይነቶች ሆነዋል ። እነዚህ ሚዲያዎች ለሰዎች የሁለትዮሽ መረጃ ልውውጥ አመቺና አሳታፊ ከመሆናቸው ባሻገር ወጪ ቆጣቢ፣ ፈጣንና ታላሚ የህብረተሰብ ክፍልን በመለየት መልዕክት ማሰተላለፋቸው በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በአገራችን በርካታ ወጣቶች በየኢንተርኔት ቤቶች አሊያም ሞባይላቸው ላይ ፌስ ቡክ ላይ ተጠምደው ይታያሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ ማህበራዊ ሚዲያዎች የጥቅማቸውን ያህል ጉዳትም አላቸው እየተባለ ነው፤ አንዳንዴ የሃሰተኛ መረጃዎች ማሰራጫ እየሆኑ መምጣቸውም ይስተዋላል ፤ በመንግስትና የግል ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞችም እነዚህ ሚዲያዎች ላይ ተጠምደው በመዋል ስራቸውን በአግባቡ የመወጣትን ጉዳይ ችላ ሲሉ ይስተዋላል፤ ፡፡በቅርብ የወጡ ጥናቶች ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት ጊዜን ማሳለፍ ለድብርት ያጋልጣል ይላሉ። ለመሆኑ በእነዚህ አዳዲስ ሚዲያዎች በተለይም በአገራችን በሰፊው ጥቅም ላይ የዋለው ፌስቡክ ነውና ፤ በፌስቡክ ምን ያህል ተጠቀምን? ምን ያህልስ ተጎዳን? ፌስቡክ አጠቃቀምን በተመለከተ ከማን ምን ይጠበቃል?

የቱን እንመን? እውነተኛውን ወይስ በሃሰት የተፈበረከውን መረጃ?

Mon Mar 28 13:27:42 GMT 2016


ሃሳብዎን ያካፍሉን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ መረጃዎች በተለያዩ የመረጃ አውታሮች ይሰራጫሉ፡፡ በእነዚህ የመረጃ አውታሮች ትክክለኛና የተዛቡ መረጃዎች ሊሰራጩ ይችላሉ፡፡ በአገራችን ውስጥ አንዳንዴ መደበኛ በሆነ መልኩ በተለያዩ የአገር ውስጥና ከውጭ ሚዲያዎች ከሚተላለፉት መረጃዎች ውጭ በማህበረሰቡ ውስጥ በሐሜት መልክ ይሁን በሌላ መልክ ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች በማህበረሰቡ ውስጥ ሲሰራጩ ይስተዋላሉ፡በተለይ በሶሻል ሚዲያ ያልሆነና ያልተፈጠረ ነገር ለምሳሌ እገሌ አረፉ፤ ከወራት በኋላ የሆነ ነገር ሊሆን ነው፣ ወዘተ የሚሉ ሃሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ይታያሉ፡፡ ለመሆኑ መረጃን ከትክክለኛ ምንጭ ብቻ መውሰድና መጠቀም እንዴት ይቻላል? ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው አሉታዊ ተጽዕኖ ምንድን ነው ፤በማህበረሰባችን ውስጥ ከትክክለኛ የመረጃ ምንጮች ከተገኙ መረጃዎች ውጭ ሰዎች ሲገናኙ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግለሰባዊ ትንተና ሲያቀርቡ፣ እገሌ እንዲህ ነው እንደዚያ ነው ብለው ሲያሙ ብዙ ጊዜን ያጠፋሉ፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግር መንስዔና መፍትሔ ምንድን ነው ብለው ያስባሉ? ከማን ምን ይጠበቃል? እስቲ እንወያይ ፤

የመልካም አስተዳደር ችግሮች በአገሪቱ አጠቃላይ እድገት ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ምንድን ነው? ችግሮቹ እንዲቀረፉ ከመንግስትና ከህዝብ ምን ይጠበቃል?..

Tue Mar 22 15:10:24 GMT 2016


ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በመልካም አስተዳደርና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከምሁራን ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በውይይታቸው የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ድህነትና ኋላቀርነትና ሌሎች ጉዳዮች ተዳስሰዋል፡፡ ለመሆኑ በአገሪቱ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ድህነትና ኋላቀርነት በአገሪቱ አጠቃላይ እድገት ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ምንድን ነው? ችግሮቹ እንዲቀረፉ ከመንግስትና ከህዝብ ምን ይጠበቃል? እስቲ በዚህ ጉዳይ ላይ እንወያይ ፤

የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የአሸናፊ ክልሎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች የዋንጫ ባለቤት ከመሆን በዘለለ ለአገራዊ መግባበት ያለው አስተዋጽኦ ምንድን ነው?

Mon Mar 21 06:54:21 GMT 2016


እስቲ እንወያይ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል አዘጋጅነት በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ለመሆኑ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የአሸናፊ ክልሎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች የዋንጫ ባለቤት ከመሆን በዘለለ ለአገራዊ መግባበት ያለው አስተዋጽኦ ምንድን ነው? ክልሎቻችን ባህላቸውንና ልምዳቸውን እንዲለዋወጡ ያለው ሚናስ ምንድን ነው ብለው ያስባሉ? ተተኪና በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያን ባንዲራ የሚያነሱና የኢትዮጵያን ስም የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ከመፍራት አንፃርስ? የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሚና ደግሞ በዚህ ውስጥ ምን መሆን አለበት ይላሉ?ሃሳብዎን ያካፍሉን ፤

እስቲ እንወያይ- በአገራችን_አሁን እየታየ ላለው የትምህርት ጥራት ጉድለት መንስኤ ምንድነው? ለመፍትሄውስ ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ?

Thu Mar 17 09:10:36 GMT 2016


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ከአገሪቱ ምሁራን ጋር ሰሞኑን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ውይይቱ ካተኮረባቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የትምህርት ጥራትን ማሻሻል አንዱና ዋነኛው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት የአገሪቱ የትምህርት ጥራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት ባለፉት አመታት የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ባደረገው ጥረት በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአገራችን ተገንብተው ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች እያሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡ይህ ከሆነ ታድያ የአገሪቱ የትምህርት ጥራት እንዴት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ሊባል ቻለ? ለመሆኑ አሁን አሁን እየታየ ያለው የትምህርት ጥራት መጓደል መንስኤ ምንድነው? ለመፍትሄውስ ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ? በዚህ ረገድ ከመንግስት ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ከሲቪክ ማህበራትና አጠቃላይ ከህብረተሰቡስ ምን ይጠበቃል ትላላችሁ? እስቲ እንወያይ

በየትኛው የመንግስት ተቋም ምን አይነት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ገጠመዎት?አስተያየትዎን ያካፍሉን

Sat Mar 12 08:24:44 GMT 2016


በፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤቶችና በክልሎች እየተካሄደ ያለው የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ትክክለኛ መፍትሄ የሚያገኘው መንግስትና ዜጎች በጋራ በሚያደርጉት ትግል ነውና ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ሃሳብዎን በነጻነት ያካፍሉን፡፡ አስተያየትዎ አገልግሎት ፈልገው በሄዱበት የመንግስት ተቋም ኃላፊው ስብሰባ ላይ ናቸው፤ ሌላ ቀን ይመለሱ የሚፈለግበዎትን ነገር አላሟሉም ይህ ይቀራል፣ ያ ይቀራል፣ ሰኞ፣ ማክሰኞ ወዘተ… እያሉ ማጉላላት ነው? ዘመድ ማስቀደም ወይም በትውውቅ መስራት ነው? በነፃ ማግኘት የሚገባዎን አገልግሎት በገንዘብ ይግዙ ነው የተባሉት ? ወይስ ሌላ? ብቻ ሃሳብዎን ያካፍሉን

መንግስት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የጀመረውን ጥረት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማከል ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል

Thu Mar 10 13:37:57 GMT 2016


ክቡር ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ በፓርላማ ለተወካዮች ምክርቤት አባላት ባደረጉት ንግግር ላይ መልካም አስተዳደር ለማስፈን የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠል መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት አስመልክተው “መንግስት የመልካም አስተዳደር መርሆዎች የሆነው የመንግስትን አሰራር ግልጽ የማድረግ መርህ ላይ በመመስረት ግልጽነት እንዲሰፍንና ችግሩ ከህዝቡ የተደራጀና የነቃ ተሳትፎ ውጭ በጭራሽ እንደማይፈታ በማመን የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ የአሳታፊነትን መርህ ተከትሎ መስራት ጀምሮአል፤ ይህ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉ ከውስጣችንም ሆነ ከውጭ የጥቅም መረቦች በተለያዩ ቦታዎች እንደታየው መወራጨትን ማስከተሉ የማይቀር ቢሆንም በምንም መልኩ ግን ትግሉ ሳይቀለበስ እንዲቀጥል ማድረግ ይገባናል” በዚህ ላይ ያለዎትን ሃሳብ ያካፍሉን ፤ አስተያየትዎን በተጨማሪም በኢቢሲ ብሎግ http://www.ebc.et/web/guest/blog ሊንክን በመጫን ሊያካፍሉን ይችላሉ

መንግስት በመልካም አስተዳደር ችግር ላይ የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፤ በዚህ ዙሪያ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማከል ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምን መደረግ አለበት ይላሉ?

Fri Mar 04 14:07:15 GMT 2016


መንግስት በመላ አገሪቱ የመልካም አስተዳደር እጥረት እንዳለ በማመን የችግሩን ምንጭና መፍትሄውን ለይቷል፤ በዚህ መሰረትም የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማረጋገጥ ለችግሩ ምንጭ የሆኑትን የአሰራርና የስርአት ማስተካከል በአጥፊዎችም ለይ በየደረጃው የአቅም ክፍተት ያለበትን በማሰልጠንና በማስተማር ፣ የማሸጋሸግ ስራ በመስራት ፣ ወደ ህግ የሚቀርቡትንም ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ሰፊ ንቅናቄ ተፈጥሮዋል ፤ በዚህ ዙሪያ ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምን መደረግ አለበት? በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳንድ የተቃዋሚ ሃይሎች እይታ ግን ስርአቱን የማስወገድ አሊያም የጥምር መንግስት እንዲመሰረት ይጠይቃሉ ፤ ይህ ከህገመንግስታዊ ስርአቱ አንጻር ሲቃኝ እንዴት ይታያል?

ወጣቱ ትውልድ የጸረ ድህነት ትግሉን ይበልጥ በማቀጣጠል የአድዋን ድል በድጋሚ ሊያስመዘግብ ይገባል እንላለን፤ እስኪ በዚህ ላይ ያለዎትን ሃሳብ እርስዎም ያካፍሉን፤

Thu Mar 03 12:13:47 GMT 2016


ከኢትዮጵያውያን አልፎ ለመላው ጥቁር ህዝቦች መነቃቃትን የፈጠረው የአድዋ ድል በኢትዮጵያ ብዝሃነት ውስጥ ያለውን ጠንካራ አንድነት ጉልህ ፋይዳ ማሣያ ነው፤ የአድዋ ድል አገራችንን የፀረ ቅኝ ግዛትና የጥቁር ህዝቦች ድልና ተምሳሌት እንዳደረጋት ሁሉ ወጣቱ ትውልድ በአገሪቱ የተጀመረውን የጸረ ድህነት ትግል ይበልጥ በማቀጣጠልም የአድዋን ድል በድጋሚ ሊያስመዘግብ ይገባል፤ እስኪ በዚህ ላይ ያለዎትን አስተያየት እርስዎም ያካፍሉን፤ አስተያየትዎን አዲስ በተከፈተው የኢቢሲ ብሎግ http://www.ebc.et/web/guest/blog ሊያካፍሉን ይችላሉ

በአገራችን ያለውን ሰላምና ልማት በአስተማማኝ መንገድ ለማስጠበቅ ከፖለቲካ አመራሩ፣ ከመንግስት መዋቅሩና ከህዝቡ ምን ይጠበቃል ?

Tue Mar 01 06:59:34 GMT 2016


በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተነሳው ሁከትና ብጥብጥ የሻዕቢያ መንግሥትና በሌሎች የውጭ ኃይሎች ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች ብሔር ብሔረሰቦች በትግላቸው ያረጋገጧቸውን መብቶች ጭምር የሚንዱ ከመሆናቸው ባሻገር ዓላማቸውም የተዳከመችና የተበታተነች ኢትዮጵያን መፍጠር ነው ፤ በመሆኑም እነዚህን ሃይሎች ሕዝቡ ሊታገላቸው ይገባል ሲሉ ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም መግለቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ መነሻነት በአገራችን ያለውን ሰላምና ልማት በአስተማማኝ መንገድ ለማስጠበቅ ከፖለቲካ አመራሩ፣ ከመንግስት መዋቅሩና ከህዝቡ ምን ይጠበቃል ይላሉ ? አስተያየትዎን ያካፍሉን