86ኛው የአውሮፓ የቅንጡ መኪኖች ኤግዚብሽን በሲውዘርላንድ ጄኔቫ ተከፈተ

የካቲት 24፣ 2008

86ኛው ትልቁ የአውሮፓ የመኪኖች ኤግዚብሽን ከ200 ዓይነት በላይ እጅግ ውድና ቅንጡ መኪኖችን በሲውዘርላንድ ጄኔቫ ለእይታ አቅርቧል፡፡

የመኪና አምራቾች በፍጥነትና በቴክኖሎጂ አሉን የሚሏቸውን አዳዲስ መኪኖች ለእይታ ያቀረቡበት ኤግዚብሽኑ የብዙዎችን እይታ ስቧል፡፡

በኤግዚብሽኑ ላይ 2.5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣው ቡጋቲ ካይሮን መኪና፣ በስፔክተር ፊልም ላይ ጀምስ ቦንድ ያሽከረከረው አስቶን ማርቲን DB፣ የእንግሊዞቹ ኩራት የሆነው ሮልስ ሮይስ ጎት ብላክ ቤጅ፣ ላምቦርጊኒ ሲንትራኒዮ፣ ፌራሪ GTC4 ሉሶ፣ ማዜሬቲ ሊቬንት SUV፣ ቤንትሊ፣ ፖርሽ እና ጃጉዋር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ