ቻይናዊያን ላጤዎች ቀናቸውን ለማክበር በአንድ ቀን ብቻ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ የሚስተካከላቸው አልተገኘም

ህዳር 02፤2010

ቻይናዊያን ላጤዎች የላጤዎች ወይም ያላገቡ ሰዎች ቀንን ለማክበር በኢንተርኔት ባደረጉት ግብይት በአንድ ቀን ብቻ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

ይህም በአለማችን በአንድ ቀን በኢንተርኔት ግብይት ከፍተኛ ወጪ በማድረግ የማይስተካከለው ክስተት ሆኗል፡፡

ይህ የላጤዎች ቀን ከባለፈው ዓርብ እኩለ ሌሊት ጀምሮ መከበር እንደሚጀምር ነው የተነገረው፡፡

የቻይና ግዙፉ የኢንተርኔት ግብይት ተቋም አሊባባ እንሚለው ከሆነ ከዚሁ ጊዜ አንስቶ እስከ ቅዳሜ ምሽት ድረስ በአሊባባ የተገበያዩት ደንበኞች ከ130 ቢሊዮን ዩዓን ወይ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርገዋል፡፡

አሊባባ ባለፈው ዓመት በዚሁ ጊዜ ያገኘው ግብይት ከ120 ቢሊዮን ዩዓን በላይ ሲሆን ይህም ክብረወሰን ሆኖ ነበር የተመዘገበው፡፡

ከአሜሪካውያን ጋር ሲወዳደርም በምስጋና እና ጥቁር አርብ ክብረ በዓል ላይ  በአንድ ቀን በኢንተርኔት ግብይት ያወጡት ወጪ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ አልሆነም፡፡

ቻይናዊያን የኮሌጅ ተማሪዎች በፈረንጆቹ 1990ቹ ውስጥ የፍቅር አጋር የሌላቸው ሰዎችን ለማስታወስ የጀመሩት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ