የዓለማችን የመጀመሪያው መንግስት አልባ ተንሳፋፊ ከተማ ሊገነባ ነው

ህዳር 5፤2010

የሰው ልጅን ከፖለቲካው ዓለም ነጻ ባደረገ መልኩ የዓለማችንን ተንሳፋፊ ከተማን በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ በ2020 ለመገንባት ታቅዷል፡፡

ይህ ተንሳፋፊ ከተማም እንደ አንድ ሃገር ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን ለሰው ልጅ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ የሚይዝ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡

ሲእስቲዲንግ ኢንስቲቲዩት በተባለ ተቋም የሚገነባው ይሄ ተንሳፋ ከተማ ውብ ሆቴሎችን፤ መኖሪያ ቤቶችን፤ ምግብ ቤቶችንና ሌሎችንም ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ከተማዋ በዓለም አቀፍ የውሃ ክልል ውስጥ የምትገነባ ሲሆን ከማንም ሀገር መንግስት ነጻ በሆነ መልኩ በራሷ ህግ የምትተዳደር ትሆናለች፡፡

የሃሳቡ ባለቤቶች በዚህ ብቻ የሚወሰኑ ሳይሆን በፈረንጆቹ 2050 በሺዎች የሚቆጠሩ ተመሳሳይ ተንሳፋፊ ከተማዎችን ለመገንባት ወጥነዋል፡፡

ሲእስቲዲንግ ኢንስቲቲዩት እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥም ለስራው የሚያስፈልገውን 60 ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ እየሰራሁ ነኝ ብሏል፡፡

ከተማው የሚገነባበት አካባቢም ታሂቲ የምትባል አነስተኛ ደሴት ሲሆን 118 ደሴቶች ተጠቃለው ይህቺን ሃገር መስርተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ወደ ተግባር ከመግባቱ በፊት ግን የፈረንሳይና የአካባቢውን መንግስት ፍቃድ ማግኘት ይጠይቃል፤ ምክንያቱ ደግሞ የፈረንሳይ መንግስት የግዛቱ ባለቤት ነውና፡፡

ምንጭ፡ ዴይሊሜይል