ወይና ወንድወሰን በመላ አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት ላይ በሁለት ዘርፎች እጩ ሆናለች

ጥቅምት 24፣ 2010

ኢትዮጵያዊቷ ወይኗ ወንድወሰን በመጪው ጥቅምት 30/2010 በናይጄሪያ ሌጎስ በሚከናወነው የመላ አፍሪካ የሙዚቃ ሽልማት ላይ በሀለት ዘርፎች እጩ ሆና ተመርጣለች፡

ወይና እጩ የሆነችበት ስራዋ "ዩ አር ኖት አሎን"/ "You are not alone" በሚለው ነጠላ ዜማዋ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት አርቲስት /Best Female Artist East Africa/ እና በሴት አርቲስት የተሰራ ምርጥ ተስፋ ሰጪና አስተማሪ ሙዚቃ /Best Female Artist Inspirational Music/ ዘርፎች እጩ ሆና ትቀርባለች፡፡

ይህ የሙዚቃ ስራዋ በሴቶች ላይ በሃገር ውስጥ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለማስቀረትና የህጻናት መብት ብዝበዛ ላይ ግንዛቤ ማስጨበት ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

የሙዚቃ ክሊፑ በዬትኛውም አካባቢ የሚገኙ የሃገሬ ሴቶች የእኩል መብት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና በእነሱ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም ያለውን ድጋፍ ያሳያል ብላለች፡፡

እናም የሃገሬ እናቶች፤ እህቶችና ህጻናት  ብቻችሁን አይደላችሁም በርቱ እያለች ነው ወይኗ፡፡

ወይና ይህን ሽልማት እንድትቀዳጅ ከታች ያለውን ሊንክ በመቻን ድምጽ በመስጠት ይደግፏት፡፡

https://goo.gl/cErF4T and https://goo.gl/rFmMG5

ምንጭ፡ ውጭ ጉዳይና አፍሪማ