በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የኢትዮጵያዊያኑ መስቀል ክብረ በዓል

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያዊያን  ዘንድ የሚከበረው መስከረም ፲፯ (17) ነው። ይህም በዓል  በድምቀት ይከበራል። 

የመስቀል በዓል አከባበር እና ቋንቋ በብሄረሰቦች

የመስቀል በዓል እንደየ ብሄረሰቡ አካባቢና ቋንቋ የተለያየ ስያሜ አለው፡፡ ለምሳሌ በሃድያ፣ በወላይታ፣ በዳውሮና ጋሞ "መስቀላ"፣ በከንባታ "መሳላ" ፣በየም "ሄቦ" በጉራጌ "መስቀር" ፣ በኦሮሞ "ጉባ" ወይም "መስቀላ" በከፊቾ እና ሻኬቾ "መሽቀሮ" በመባል ሲታወቅ በአማራና ትግይ ደግሞ የመስቀል በዓል ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህም እንደየ አካባቢው ራሱን የቻለ ባህላዊ ቅርፅ መያዙን የሚያሳይ ነው።

የደመራ ስነ ስርዓት

በሀገራችን የደመራ ስነ ስርዓት ከቦታ ቦታ ይለያያል። በትግራይ፣ በላስታና ላሊበላ፣ በአክሱም፣ በሰሜንና በደቡብ ወሎ ፣ በዋግህምራ፣ በጎጃምና አዊ ዞን ደመራው መስከረም 16 ቀን ቢደመርም ስርዓተ ፀሎቱ የሚካሄደውና ደመራው የሚለኮሰው መስከረም 17 ቀን ንጋት ላይ ነው፡፡ በአንፃሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በሸዋና በከፊል ጎጃም ደመራው የሚበራው /የሚሎከሰው/ መስከረም 16 ቀን ምሽት ነው፡፡

የደመራ በዓል በብሄራዊ ደረጃ የሚከበረው

በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ሲሆን እዚህ ደመራ የሚደመረውና ስርዓቱ ፀሎት ተደርጎ የሚቀጣጠለው መስከረም 16 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ማታ ነው፡፡

መስቀል ክብረ በዓል- በዓለም የቅርስ መዝገብ በ2006 ዓ.ም በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ በተካሄደ 8ኛው የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የትምህርትና ባህል ማዕከል /UNESCO/ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያዊ የመስቀል በዓል አከባበር በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ 

የመስቀል በዓል አከባበር በዓለም አቀፍ ደረጃ የመመዝገቡ ፋይዳ

የመሰቀል በዓል አከባበር በዓለም አቀፍ ደረጃ የመመዝገቡ ፋይዳ ቅርሱን የተመለከቱ መረጃዎች በዩኔስኮ ድረ ገጽ ላይ የሚለቀቅ በመሆኑ ሀገረ አቀፍና ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ እንደሚረዳው፤ የቱሪስት መስህብ መሆኑ፤ ከቀድሞ በተሻለ እንክብካቤ የሚደረግለትና ለትውልድ እንዲተላለፍ እገዛ ማድረጉን፤ ዓለም አቀፍ አጥኝዎችና ተመራማሪዎችን መሳቡ ዋና ዋናዎቹ ጥቅሞች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ስመዘገበቻቸው ዘጠኝ ታዳሽ ዓለም አቀፍ ቅርሶች

የሰሜን ተራሮች፤ አክሱም ጸዮን ሐውልቶች፤ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፤ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፤ ጢያ ትክል ደንጋዮች፤ የታችኛው አዋሽ ሸለቆ፤ ሐረር ጀጎል፤ የኮንሶ ባሕላዊ መልክአ ምድር እና የፋሲል ግንብ ኢትዮያ ከዚህ ቀደም ያስመዘገበቻቸው የሚዳሰሱ (tangible) ቅርሶች ናቸው፡፡

የመስቀል በዓል አከባበር እና ፍቼ ጨምባላላ የማይዳሰሱ ቅርሶች  ተብለው ከተመዘገቡት የኢትዮጵዮጵያዊያን ሀገር በቀል ህዝባዊ ሀብቶች ባዕላት ናቸው፡፡

 

የ2008 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር

ምንጭ፡-የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን

አዘጋጅ፡- ሀና ግርማ

ፎቶ ሪፖተር፡-ናትናዔል ፀጋዬ /2008/