በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገለፀ

5 Mons Ago 591
በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገለፀ

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት ስራ የጀመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል፡፡

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም ባንኩ ገልጿል።፡፡

በባንኩ ሲስተም ችግር ምክንያት የተቋረጠውን አገልግሎት መልሶ ለማስጀመር ጥረቱ መቀጠሉን እና የባንኩ የቅርንጫፎች አገልግሎት ወደ ስራ መመለሱን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኃ/እየሱስ በቀለ ለኢቢሲ ሳይበር ገልፀዋል፡፡

በባንኩ ሲስተም ችግር ምክንያት የወጣ ገንዘብ ስለመኖሩ ኢቢሲ ሳይበር ላቀረበዉ ጥያቄ፤ ምክትል ፕሬዝዳንቱ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ የማጣራት እና የምርመራ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አጠቃላይ የምርመራው ስራ እንደተጠናቀቀም ጉዳዩ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ማስታወቁን ዛሬ መግልፁ ይታወሳል፡፡

የባንኩ ቅርንጫፎች አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር እና ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ለማስጀመር በከፍተኛ ርብርብ እየተሰራ መሆኑን የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኃ/እየሱስ በቀለ ገልፀዋል፡፡


Feedback
Top